Sunday, September 22, 2024
spot_img

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከጦርነት አካባቢ የተፈናቀሉ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጥቅምት 24 2014 ― በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከጦርነት አካባቢ የተፈናቀሉ ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታውቋል፡፡

ይህንኑ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስለሺ ተመስገን እንደነገሩት ዶይቸ ቬለ ዘግቧል፡፡

እንደ ኃላፊው ከሆነ ዞኑ 10 ሺሕ ተማሪዎችን ለመቀበል የተዘጋጀ ቢሆንም፣ ባለው የመንገድ ችግርና ጦርነቱ ባሳደረው ተጽዕኖ እስካሁን የመጡት ተማሪዎች ከአንድ ሺህ አይበልጡም፡፡

አብዛኞቹ ተማሪዎችም ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዳህና ወረዳ እና ከወልዲያ የመጡ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ስለሺ፣ በዋናነት በሁለት እጁ እነሴ፣ በእነብሴ፣ በጎንቻና ጎዛምን ወረዳዎች፣ በደብረማርቆስ፣ በቢቡኝና ሞጣ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እየተማሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሁንም ዞኑ ተማሪዎችን እየጠበቀ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ ተማሪዎችም በተቻለ መጠን የትምህርት ማስረጃቸውን ይዘው እንዲመጡ አሳስበዋል፡፡

የተማሪዎቹን ወጩ በተመለከተም የዞኑ አመራሮች፣ ባለሀብቶችና ግለሰቦች ወጪውን ሸፍነው በመማር ላይ መሆናቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ የደብረማርቆስ ነዋሪ የሆኑ ግለሰቦችም ተማሪዎቹን በቤታው ተቀብለው ማስተናገዳቸው ተጠቅሷል፡፡

በዛሬው እለት አንድ ዓመት በደፈነው በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን እዝ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀው ጦርነት፣ የሕወሓት ኃይሎች በመግፋታቸው በተለይ በሰሜን ወሎ አካባቢዎች ትምህርት መቋረጡ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img