Saturday, November 23, 2024
spot_img

የሕወሓት ኃይሎች ደሴ ከተማን ተቆጣጥረናል ማለታቸው ተዘገበ

– የፌዴራል መንግሥት በበኩሉ ደሴ በመከላከያ ቁጥጥር ስር መሆኗን በመግለጽ “አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙሃን የሽብር ቡድኑን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ” ብሏል

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥቅምት 20፣ 2014 ― የሕወሓት ኃይሎች ደሴ ከተማን መቆጠጠራቸውን መናገራቸውን ሬውተርስ፣ አዣንስ ፍራንስ እና አልጀዚራ የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳን እና አናግረናቸዋል ያሏቸውን ነዋሪዎች ጠቅሰው ዘግበዋል።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ ደግሞ አሁንም ደሴና አካባቢዋ “በፀጥታ ሃይላችን ስር ነው” ያለ ሲሆን፣ “ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ” መጥቷል ያለው የሕወሃት ኃይል “በመመከት አኩሪ ገድል” እየተፈፀመ ይገኛል ሲል አክሏል።

አያይዞም “አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙሃን የሽብር ቡድኑን የሃሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ” ያለው የኮሚኒኬሽን አገልግሎቱ፣ “በወሬ የሚያዝ ከተማ የለም ሊኖርም አይችልም” በማለት፣ በተለይ ያልተጣራ መረጃን በመያዝ “ህዝብን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙና የሽብር ቡድኑ መጠቀሚያ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ” ሲል አሳስቧል።

ሬውተርስ የሕወሃት ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ ካልታወቀ ቦታ በሳተላይት ስልክ ደሴን ተቆጣጥረን ወደ ኮምቦልቻ እያቀናን ነው ብለውኛል ሲል አስነብቧል።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት አገርሽቶ በከፍተኛ ሁኔታ የቀጠለው የፌዴራል መንግስት እና የሕወሃት ኃይሎች ጦርነት በሚቀጥለው ሳምንት አንድ ዓመት ይደፍናል።

ባለፉት ቀናት የፌዴራል መንግሥት ወደ መቐለ ከተማ የአየር ላይ ጥቃቶችን ማድረጉን በተደጋጋሚ አሳውቋል። የሕወሓት ኃይሎቾ በበኩላቸው ወደ ደሴ ከተማ የመድፍ አሩር መተኮሳቸው ሲነገር ነበር። በሁለቱም በኩል በተሰነዘሩ ጥቃቶች ንጹሐን ሕይወታችው መነጠቁን መረጃዎች ጠቁመዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img