Tuesday, November 26, 2024
spot_img

መቐለ የሚገኘው መሥፍን ኢንጅነሪንግን በአየር መምታቱን መንግሥት አስታወቀ

  • ጥቃቱ መሰንዘሩን የሕወሓት ቃል አቀባይ አረጋግጠዋል

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 18፣ 2014 ― የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ክልል መቀመጫ የሚገኘውን መስፍን ኢንጅነሪንግ ሁለተኛው ክፍል በአየር መምታቱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል፡፡

የኮሚኒኬሽን አገልግሎቱ ይህ ተቋም ሕወሐት ወታደራዊ መሣሪያዎችን የሚጠግንበት ቦታ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

የሕወሓት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ጥቃት መሰንዘሩን አረጋግጠው፣ የአየር መከላከያ ኃይላቸው እየተዋጋ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

አንድ ዓመት ሊደፍን ጥቂት ቀናት የቀሩት በትግራይ ጀምሮ ወደ አጎራባች ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት አገርሽቶ ሲቀጥል፣ የፌደራል መንግሥት ካለፈው ሳምንት ሰኞ ጥቅምት 8፣ 2014 ጀምሮ በተከታታይ በመቐለ ከተማ የአየር ጥቃት እየተፈጸመ መሆኑን ሲያሳውቅ ቆይቷል፡፡

መንግሥት በተደጋጋሚ የሰነዘራቸው የአየር ጥቃቶ ኢላማ የሚያደርጉት በሕዝብ ተወካዮ ምክር ቤት በሽብርተኛነት የተፈረጀው ሕወሓት ለወታደራዊ አገልግሎት የሚጠቀማባቸው ሥፍራዎችን እንደሆነ ገልጧል፡፡ ነገር ግን በሕወሓት በኩል በጥቃቱ ንፁሐን ጉዳት እንደደረሰባቸው ይገልጻል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ፋብሪካዎች እና ሆስፒታል መውደሙንም ነው ያመለከተው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img