Tuesday, November 26, 2024
spot_img

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ለሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲፈለግለት ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 18፣ 2014 ― የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር ኃላፊ በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አስቸኳይ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡

የዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ኃላፊ ፒተር ሞውረር ባለፉት ሦስት ቀናት በኢትዮጵያ ቆይታ አድርገዋል፡፡ በዚህ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው ከጦርነቱ ጋር ተያይዞ ስላው የሰብአዊ አቅርቦት መምከራቸውን ቀይ መስቀል በድረ ገጹ አስታውቋል፡፡

ፒተር ሞውረር ቆይታቸውን ሲያጠናቅቁ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እየተደረገ ያለው ጦርነት የሰብአዊ እርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር በየቀኑ እንዲጨምር እያደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ በጦርነቱ ተሳታፊ ለሆኑ አካላት መልዕክቱ ሁሌም ተመሳሳይ ነው፤ ለችግሩ አስቸኳይ ፖለቲካዊ መፍትሔ መስጠት ከግጭት ያወጣናል›› እንዳትም ቢቢሲ አስነብቧል፡፡

አክለውም ግጭቱ በፍጥነት ቢቆም እንኳን ከቀያቸው የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መዘንጋት የለብንም ሲሉ አሳስበዋል።

አንድ ዓመት ሊደፍን በተቃረበው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እስከ 5.2 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች ትግራይ ውስጥ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል። በተጨማሪም ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሏል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img