Monday, November 25, 2024
spot_img

የመንግሥታቱ ድርጅት የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ አካላት ጦርነቱን እንዲያቆሙ በድጋሚ ጠየቀ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ ጥቅምት 12 2014 ― የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በሚካሄደው ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ግጭት እንዲያቆሙ በድጋሚ ጠይቋል፡፡

በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ቃል አቀባይ ፋረሃን ሃቅ ‹‹በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ተጨማሪ ጉዳቶችን እና በሲቪሎች ላይ የሚደርሰውን ስቃይ ለማስቀረት የግጭቱ ተሳታፊ አካላት ከግጭት እንዲቆጠቡ ጥሪያችንን ደግመን እናሰማለን›› ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ፋረሃን ሃቅ አክለውም ‹‹በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ሕጎችን ማክበር አለባቸው፤ ንፁሑሃን ዜጎችን እና መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ›› እንዳለባቸውም ገልጸዋል፡፡

በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ከሰሞኑ አገርሽቶ በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠሉ ሲነገር፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይልም በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ ትላንትናን ጨምሮ ለሦስት ጊዜያት ጥቃት መፈጸሙን አስታውቋል፡፡

በነዚህ ጥቃቶች የሦስት ንጹሐን ሕይወት መቀጠፉን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ማስተባበሪያ ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫው አመልክቷል፡፡ የአየር ጥቃቱን በተመለከተ የተናገሩት ሀርሃን ሀቅ ሰሴቶች እና ሕፃናት ሰለባ መሆናቸውን ሰምተናል ብለዋል፡፡

ለአንድ ዓመት በተቃረበው ጦርነት የፌደራል መንግሥት ተቆጣጥሮት ከነበረው ትግራይ ክልል የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ አውጆ ከትግራይ አካባቢዎች መውጣቱን ተከትሎ፤ የሕወሃት ኃይሎች ወደ መቐለ በመመለስ፣ የክልሉን ድንበር አልፈው አጎራባች የአፋር እና አማራ ክልሎችን መቆጣጠራቸው ይነገራል፡፡ የሕወሃት ኃይሎች ይዘዋቸዋል ከሚባሉት መካከል የሰሜን እና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ይገኙበታል፡፡

የሕወሃት ኃይሎች ከያዟቸው አካባቢዎች መካከል ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ጭፍራ እና በአማራ ክልል ውጫሌ በንጹሐን ላይ ግድያ መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች ወጥተዋል፡፡

ይህንኑ ተከትሎም ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ዋግኽምራ እንዲሁም ከአፋር አካባቢዎች በርካቶች ተፈናቅለዋል። የተመድ ምክትል ቃል አቀባይ ፋረሃን ሃቅ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የግጭቱን መስፋፋት ተከትሎ በአማራ እና አፋር የሰብዓዊ እርዳታ ፈላጊ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን አስታውሰዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img