Monday, September 23, 2024
spot_img

በመቐለ በሳምንቱ ሦስተኛው የአየር ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ ጥቅምት 11፣ 2014 ― የትግራይ ክልል ዋና መቀመጫ መቐለ በተያዘው ሳምንት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የአየር ጥቃት ማስተናገዷ ተነግሯል።

ሬውተርስ የዜና ወኪል የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ኃላፊው አቦ ለገሰ ቱሉ ዛሬ ሐሙስ የአየር ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠውልኛል ሲል ዘግቧል።

የዛሬው የአየር ድብደባ ኢላማ ያደረገው የቀድሞ የአገር መከላከያ ሠራዊት ይዞታ የነበረና በአሁኑ ጊዜ የሕወሓት ኃይሎች የማሰልጠኛ ማዕከል መሆኑን ቃል አቀባዩ መግለጻቸውን የዜና ወኪሉ አስነብቧል።

የዛሬው የአየር ጥቃት ከሰዓት ከዘጠኝ ሰዓት በኋላ የተፈፀመ ነው ተብሏል።

በጥቃቱ የደረሰ ጉዳትን በተመለከተ እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ባለፈው ሰኞ እና ትላንት ረቡዕ ጥቅምት 11 በተመሳሳይ ወደ መቐለ የአየር ጥቃት መሰንዘሩ መነገሩ ይታወሳል።

በቀደሙት ጥቃቶች የንጹሐን ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል።

ጋብ ብሎ የነበረው ጦርነት ከሰሞኑ ተባብሶ መቀጠሉን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በጦርነቱ ከአገር መከላከያ ሠራዊትም ሆነ ከሕወሃት በኩል ድል እያስመዘገቡ ስለመሆኑ ሁለቱም ይገልጻሉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img