Sunday, September 22, 2024
spot_img

በ50 ኢትዮጵያውያን እገታ እና ሕገ ወጥ ዝውውር የተከሰሰው ግለሰብ በደቡብ አፍሪካ ፍርድ ቤት ቀረበ

 

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ ጥቅምት 9 2014 በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ 50 ኢትዮጵያውያን ዜጎችን በማገትና በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠረው ግለሰብ ፍርድ ቤት መቅረቡ ተሰምቷል፡፡

የ50 ዓመቱ አሕመድ ካፌቾ ባለፈው ሳምንት ከ 12 እስከ 50 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 50 ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ዘካሪያ በተባለ መናፈሻ ውስጥ በማገትና ታጋቾቹ እንዲለቀቁ ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በመጠየቅ ወንጀል ነበር በቁጥጥር ስር የዋለው።

የአገሪቱ ብሔራዊ ዓቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ከእገታው የተረፉት ሰዎች ወደ ደቡብ አፍሪካ እንዴት እንደገቡና በአገሪቱ ውስጥ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ከሀገር ውስጥ ጉዳይ መምሪያ ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ለተጨማሪ ምርመራ ችሎቱ እስከ ጥቅምት 15፣ 2014 ድረስ እንዲዘገይ መደረጉን መግለጻቸው አይ ኦ ኤል የተባለው ድረ ገጽ አስነብቧል፡፡  

ከታገቱት ዜጎች ቤተሰቦች ጋር በቀጥታ የተገናኘ መሆኑንና ታጋቾቹም የት እንደሚገኙ መረጃ ማቀበሉን ያካባቢው ፖሊስ ገልጿል።

ደቡብ አፍሪካ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሕገ ወጥ መንገድ ስደት የሚሄዱባት መሆኗ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img