Friday, November 22, 2024
spot_img

በመቀሌ ከተማ በሁለት ቦታዎች የተደረገው የአየር ድብደባ ኢላማዎች የመገናኛ እና የሚዲያ ማሰራጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ ተጠቆመ

በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ በሁለት ቦታዎች የተደረገው የአየር ድብደባ ኢላማዎች የመገናኛ እና የሚዲያ ማሰራጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ ከመቀሌ ከተማ ወጣ ብሎ ከመሶበ ተራራ አቅራቢያ የተደረገው ጥቃት ያነጣጠረው ቀደም ሲል ኢንሳን እና ሬዲዮ ፋናን ጨምሮ መረጃዎችን በስፋትና በርቀት ለማስተላለፍ የሚያገለግለው የመረጃ ማሰራጫ ማዕከል ነው።

በፌዴራሉ መንግሥት ባለቤትነት ይተዳደር የነበረው የመረጃ ማሰራጫ ማዕከል በሕወሃት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ከገባ በኋላ ለወታደራዊ አላማ ጥቅም ላይ መዋሉ ለድብደባው ዋና ምክንያት ሳይሆን እንዳልቀረ ነው የተነገረው።

ሁለተኛው የአየር ድብደባ ኢላማ መቀሌ ውስጥ የሚገኘው የድምጸ ወያኔ ማሰራጫ ነው የተባለ ሲሆን፣ ተልዕኮውም በስኬት መጠናቀቁን ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዛሬ በፈጸመው ድብደባ ንጹሃን ዜጎች እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረጉንና ይህም በተሳካ ሁኔታ መፈጸሙ የተገለጸ ቢሆንም፣ የሕወሃት መገናኛ ብዙሃን በንጹሐን ላይ ጉዳት ደርሷል የሚል መረጃ አውጥተዋል።

ቀደም ብሎ በጉዳዩ ላይ የተናገሩት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ለገሰ ቱሉ ጥቃቱን አስተባብለው ነበር። ዘገባ ይዘው የወጡ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በአየር ጥቃቱ ንጹሐን መገደላቸውን ዘግበዋል።

አየር ኃይል የሰነዘራቸው ኢላማዎች በትክክል ስለመመታታቸውም ሆነ የንጹሐን ጥቃት ኢላማ መደረግ ከገለልተኛ ወገኖች ማረጋገጥ አልተቻለም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img