Sunday, September 22, 2024
spot_img

አብን የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ኃይሎች በሕወሓት ላይ ያገኙትን ብልጫ ወደ ድል እንዳይለውጡ መንግሥት ዳተኝነት አሳይቷል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ ጥቅምት 8 2014 ― የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ኃይሎች ጠላት ሲል በጠራው በሕወሓት ላይ አግኝተውታል ያለውም ‹‹ወታደራዊ ብልጫ በማጠናከር አስተማማኝ ወደ ሆነ ድል ለመለወጥ›› በመንግሥት በኩል ‹‹ዳተኝነት›› መታየቱን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ፓርቲው ይህ በመንግስት ታይቷል ያለው ‹‹ከልክ ያለፈ ዳተኝነት እንዲሁም የአመራር ክፍተት›› በሕዝቡ ላይ ‹‹ከፍተኛ ጉዳት ያስከተለ ከመሆኑም በላይ የመከዳት ስሜት ፈጥሮበት ይገኛል›› ብሏል፡፡

አብን ሕወሃት በአሁኑ ጊዜ ‹‹በተለይ በደቡብና በሰሜን ወሎ ግንባሮች የሚስተዋሉ የአመራር ክፍተቶችንና ደካማ ጎኖችን በመጠቀም ደሴና ከምቦልቻን ጨምሮ አካባቢውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ›› እንደሚገኝም ነው ያመለከተው፡፡ በመሆኑም ‹‹ጉዳዩ በሀገራዊ ማዕቀፍ ተይዟል›› በሚል ማናቸውንም እገዛ ሲጠብቅ ቆይቷል ላለው የክልሉ ሕዝብ፣ ከእንግዲህ ‹‹ተጨማሪ መዘናጋት ካሳየህ ውርደቱ ለልጅና ለልጅ ልጆችህ የሚተርፍ ይሆናል፡›› ሲል አስጠንቅቋል፡፡

አብን በመግለጫው ‹‹አማራ ነኝ የምትል ሁሉ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ ቆርጠህ ተነሳ›› ሲል ጥሪውን አቅርቧል፡፡

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ በአሁኑ ሰዓት በተለይ በወሎ በኩል አጠቃላይ ለዘረፋ፣ ለውድመትና ለጭፍጨፋ አሰፍስፏል ያለውን የሕወሃት ኃይል ‹‹ቅስም ለመስበር የሚያስችል ምሉዕ የመከላከል ስምሪት መወሰድ አለበት›› በማለት ሕዝቡን ‹‹ማናቸውንም የአዘቦት ሥራና የትምህርት እንቅስቃሴዎች ከወዲሁ በማቆም በሙሉ ኃይሉ ወረራውን ለመቀልበስ እንዲረባረብ›› ብሏል፡፡

በሌሎቹም የአማራ አካባቢዎች ወራሪ ያለው ኃይል ጥቃት በከፈተባቸው ግንባሮች ህዝቡ ለአፍታ ሳይዘናጋ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከአማራ ኃይሎች ጋር በንቃት ተባብሮ በመቆም ‹‹የማያዳግም ርምጃ እንዲወስድ›› እንዲሁም አካባቢውን ከሕወሓት ማጽዳት አለበት ነው ያለው፡፡

በሌላ በኩል አብን ዳተኝነት አሳይቷል ያለውን የፌዴራል መንግስት፣ ‹‹በፍላጎት፣ በውሳኔ ሰጭነት፣ በትጥቅና ስንቅ አቅርቦት እንዲሁም በማስተባበር ረገድ የታዩበትን ጉልህ ክፍተቶች በማረም፣ በማስተካከል፣ በብቃትና በቁርጠኝነት በመሰለፍ፣ ህዝብንና ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ የሚያስችሉ ጠንካራና ፈጣን ርምጃዎችን ወስዶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲያረጋግጥ›› ሲል አሳስቧል፡፡

ከዚሁ ጦርነት ጋር በተገናኘ የክልሉ መንግስት ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫው ሕወሃትና ግብረ አበሮቹ ‹‹ከኢትዮጵያ ምድር እስከወዲያኛው እስካልተነቀሉ ድረስ የአማራ ሕዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ህልውና በጽኑ መሰረት ላይ አይቆምም›› በማለት፣ ‹‹ከዚህ አኳያ የአማራ ሕዝብ ህልውናም ሆነ የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚረጋገጠው ትህነግ መቃብር ላይ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት›› እንደሌለበት አሳስቧል፡፡

<!– /* Font Definitions */ @font-face {font-family:”Cambria Math”; panose-1:2 4 5 3 5 4 6 3 2 4; mso-font-charset:0; mso-generic-font-family:roman; mso-font-pitch:variable; mso-font-signature:-536869121 1107305727 33554432 0 415 0;} @font-face {font-family:Calibri; panose-1:2 15 5 2 2
የአብን ሊቀመንበር አቶ በለጠ ሞላ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ከዚሁ ጦርነት ጋር በተገናኘ የክልሉ መንግስት ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫው ሕወሃትና ግብረ አበሮቹ ‹‹ከኢትዮጵያ ምድር እስከወዲያኛው እስካልተነቀሉ ድረስ የአማራ ሕዝብም ሆነ የኢትዮጵያ ህልውና በጽኑ መሰረት ላይ አይቆምም›› በማለት፣ ‹‹ከዚህ አኳያ የአማራ ሕዝብ ህልውናም ሆነ የኢትዮጵያ ትንሳኤ የሚረጋገጠው ትህነግ መቃብር ላይ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት›› እንደሌለበት አሳስቧል፡፡

ይኸው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የክልሉን ኮሚኒኬሽን ጠቅሶ ያጋራው መግለጫ፣ በሌሎች የመንግስትና የክልል መገናኛ ብዙሃን ያልተዘገበ ሲሆን፣ በመግለጫው የአማራ ክልል መንግስት የሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን ወሎና የዋግኽምራን ሕዝብ ወራሪ ካለው ሕወሃት ‹‹ነጻ ለማውጣት በሚደረገው ትግል መሳሪያ ያለው በመሳሪያው፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ትርፍ ሀብትና ንብረት ያለው በገንዘቡ፣ ሐሳብ ያለው በሐሳቡ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከሚሊሺያና ፋኖ ጎን መሰለፍ እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአሜን ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት አገርሽቷል በተባላው ውጊያ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ አቅራቢያ እየተካሄደ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

Featured Video

Toggle panel: Featured VideoPaste a video link from Youtube, Vimeo, Dailymotion, Facebook or Twitter it will be embedded in the post and the thumb used as the featured image of this post.
You need to choose Video Format from above to use Featured Video.Notice: Use only with those post templates:

  • Post style default
  • Post style 1

ይኸው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የክልሉን ኮሚኒኬሽን ጠቅሶ ያጋራው መግለጫ፣ በሌሎች የመንግስትና የክልል መገናኛ ብዙሃን ያልተዘገበ ሲሆን፣ በመግለጫው የአማራ ክልል መንግስት የሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን ወሎና የዋግኽምራን ሕዝብ ወራሪ ካለው ሕወሃት ‹‹ነጻ ለማውጣት በሚደረገው ትግል መሳሪያ ያለው በመሳሪያው፣ ጉልበት ያለው በጉልበቱ፣ ትርፍ ሀብትና ንብረት ያለው በገንዘቡ፣ ሐሳብ ያለው በሐሳቡ ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአማራ ልዩ ኃይል፣ ከሚሊሺያና ፋኖ ጎን መሰለፍ እንዳለበት ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአሜን ኢትዮጵያ ባለፉት ቀናት አገርሽቷል በተባላው ውጊያ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ አቅራቢያ እየተካሄደ መሆኑን የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱ መነገሩ አይዘነጋም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img