Sunday, July 7, 2024
spot_img

የሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪዋ ግብጽ ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ከምትፈጽመው ማንኛውም ስምምነት በፊት ከኔ ጋር ልትመክር ይገባል የሚል አቋም መያዟ ተሰማ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ ጥቅምት 6፣ 2014 ―  ከሰሞኑ ኢትዮጵያ ከቱርክ ለጦር አገልግሎት የሚውል ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ለመግዛት ማቀዷ በግብጽ ዘንድ ቁጣ መቀስቀሱን የሚያመለክቱ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ተደራዳሪዋ ግብጽ፣ ቱርክ ከኢትዮጵያ ጋር ከምትፈጽመው የትኛውንም ዐይነት ስምምነት በፊት ከኔ ጋር ልትመክር ይገባል የሚል አቋም መያዟ ተነግሯል፡፡

ሬውተርስ የዜና ወኪል ሁለት ግብጻውያን የደኅንነት ምንጮች ነገሩኝ ብሎ እንደዘገበው፣ ኢትዮጵያ እና ቱርክ ሊደርሱ የሚችሉት አንዳች ስምምነት እንዳይፈጸም አሜሪካ እና የአውሮፓ ኅብረት ጣልቃ እንዲገቡ ካይሮ ጠይቃለች።

መንግስት ይፋዊ ምላሽ ባይሰጥበትም ኢትዮጵያ ከቱርክ ለመግዛት ጥያቄ አቅርባለች የተባለው ባይራክታር ቲቢ2 የተሰኘ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውል ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ነው፡፡

የዚህ ድሮን የሽያጭ ስምምነት የመለዋወጫ አቅርቦት እና የሰው ኃይል ስልጠናን እንደሚጨመር የተገለጸ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ከቱርክ ለመግዛት ያሰበቻቸው ድሮኖች ብዛት እና ዋጋቸውን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ አልወጣም፡፡

ቱርክ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለሰሜን አፍሪካዊቷ አገር ሞሮኮ ድሮኖችን ስለመሸጧ የዘገበው ሬውተርስ፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አንድ ዲፕሎማት ሞሮኮ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ያዘዘቻቸው የመጀመሪያ ዙር ድሮኖችን መረከቧን ገልጸው፤ ኢትዮጵያም ያዘዘችው ድሮንን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ባይኖርም ቱርክ ሰራሽ ድሮኖች ባለቤት የመሆን እቅድ አላት ማለታቸውን አስነብቧል፡፡

ቢቢሲ ከቱርክ ዕቃ ላኪዎች ጉባኤ አግኝቼዋለሁ ያለውን አሃዝ ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ፣ ኢትዮጵያ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት የመጀመሪያ ሦስት ወራት ወደ አገር ውስጥ ያስገባቻቸው የመከላከያ እና አቪዬሽን ቁሶች ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከ203 ሺህ ዶላር ወደ 51 ሚሊዮን ዶላር አድርጓል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img