Monday, November 25, 2024
spot_img

ሕወሓት በያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች የአገር መከላከያ መልሶ ማጥቃት እያደረገ እንደሚገኝ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና የሰሜን ወሎ ዞን ባለስልጣናት ገለጹ

ሕወሓት በወረራ በያዛቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች የአገር መከላከያ እና የአማራ ክልል ኃይሎች የመልሶ ማጥቃት ጦርነት መጀመራቸውን የሕወሓት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ለውጭ የመገናኛ ብዙኃን ተናግረው ነበር።

ሮውተርስ የዜና ወኪል ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳን በመጥቀስ እንደዘገበው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል ኃይሎች በቅንጅት በሁሉም ግንባሮች በታጣቂዎቻቸው ላይ ጥቃት ከፍተዋል፡፡

አቶ ጌታቸው ለዜና ወኪሉ “በአማራ ክልል ወገል ጤና፣ ውርጌሳና ሐሮ በተባሉ አካባቢዎች ከምድርና ከአየር በሚተኮሱ ከባድ መሳሪያዎች በሕወሓት ኃይሎች ላይ ጥቃት ተከፍቷል” ብለዋል።

ዶይቼ ቬለ በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ተስፋዬ ገብሬን ጠቅሶ እንደዘገበው መንግስት በሕወሓት የተያዙ አካባቢዎችን ለማስለቀቅ ውጊያ ጀምሯል። በዚህም አቶ ተስፋዬ “ጠላት” ባሉት የህወሓት ኃይል ላይም ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው ብለዋል።

ቡድኑ የያዛቸውን አካባቢዎች በጦርነትም፣ ተስፋ በመቁረጥም ጥሎ እየሸሸ እንደሆነና የተስፋ ቆራጭነት ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነም ነግረውኛል ብሎ ሚዲያው ዘግቧል።

በተመሳሳይ በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን የአስተዳደርና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ኃይለማሪያም አምባዬ በበኩላቸው የሕወሓት ኃይል በሁሉም ግንባሮች በመልሶ ማጥቃት ውጊያ እየተመታ እንደሆነ መናገራቸው ተመላክቷል ነገር ግን የተጠቃለለ መረጃ ለመስጠት ጊዜው ገና መሆኑን አስረድተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img