Monday, October 7, 2024
spot_img

በግንባታ ላይ ያለው የአዋሽ ወልዲያ/ሃራ ገበያ የባቡር ሐዲድ ፕሮጀክት የሕወሓት ኃይሎች ጥቃት ኢላማ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቀ

ሚኒስቴሩ በግንባታ ላይ ያለው የአዋሽ ወልዲያ/ሃራ ገበያ የባቡር ሐዲድ ፕሮጀክት የሕወሓት ኃይሎች የጥቃት ኢላማ መደረጉን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው ያሳወቀው።

ከዚህ በተጨማሪም የሕወሃት ኃይሎች በተቆጣጠሯቸው የሰሜን ወሎ እና ጎንደር አከባቢዎች ሌሎች መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ቡድኑ ባደረሰው ጥቃት ቦታዎች ትምህርት ቤቶች፣ ኮሌጆች፣ ባንኮች፣ ጤና ጣብያዎች፣ ሆቴሎችን እና ሌሎች ተቋማት ወድመዋልም ብሏል።

ከዚህም ባሻገር ሚንስቴሩ ሕወሓት በተቆጣጠራቸው ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች ኢኮኖሚ አደጋ ከላይ መውደቁን ሪፖርት እንደደረሰው ገልጿል።

የሕወሓት ኃይሎች እና ተባባሪዎቻቸው የሆኑ አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎችን እየሰረቁ መሆኑና መውሰድ ያልቻሉትንም እያወደሙ እንደሆነ በመግለጫው ሰፍሯል።

ሚንስቴሩ የእርዳታ ማከማቻዎች መዘረፋቸው እና የአካባቢው ነዋሪዎችም የተሰጣቸውን እርዳታ በሕወሓት ሀይሎች መነጠቃቸውንም የገለጸ ሲሆን፣ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሰሜን ወሎ እና ጎንደር ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች ሰብአዊ እርዳታ እንዲያደርግ በመግለጫው ጠይቋል፡፡

ጥቃቱን በማድረስ ውንጀላ የቀረበበት ሕወሃት የሰጠው ምላሽ የለም።

በተያዘው ወር ከጀመረ አንድ ዓመት የሚደፍነው በአገር መከላከያ ሠራዊት እና በሕወሃት ኃይሎች መካከል የሚደረገው ጦርነት ጋብ ያለ መስሎ የነበረ ቢሆንም ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀናት አንስቶ መቀስቀሱን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በሰሞኑ ጦርነት ሕወሃት በተቆጣጠራቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች በመከላከያ ሠራዊት ጥቃት እየተሰነዘረበት መሆኑን በመጥቀስ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቃቱን እንዲያስቆም የሚጠይቅ መግለጫ ማወጣቱ መነገሩ ይታወሳል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img