Friday, November 22, 2024
spot_img

የአገር መከላከያ ሠራዊት የአማራ ክልል አካባቢዎችን በሚቆጣጠሩ የሕወሃት ኃይሎች ላይ የአውሮፕላን ድብደባ እያካሄደ እንደሚገኝ ተዘገበ

የአገር መከላከያ ሠራዊት የአማራ ክልል አካባቢዎችን በሚቆጣጠሩ የሕወሃት ኃይሎች እና እና ይዞታዎቻቸው ላይ የአውሮፕላን ድብደባ እያካሄደ እንደሚገኝ ከሕወሃት ቃሎ አቀባይ ጌታቸው ረዳ መስሚቱን ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአየር ድብደባው ዓላማ መጠነ ሰፊ የምድር ላይ ጥቃት ለመጀመር ነው ብለው እንደሚያምኑ ጌታቸው ረዳ መግለጻቸው በዘገባው ተመላክቷል።

አቶ ጌታቸው አክለውም መከላከያ ሠራዊት በሁሉም ግንባሮች በመድፍ እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) በመታገዝ የማጥቃት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከትላንት ሐሙስ መስከረም 27 ጀምሮ እየተካሄደ ነው የተባለው የአየር ድብደባ፣ አፋር እና አማራ ክልሎችን በሚያገናኘው መንገድ በወገልጤና እና ውርጌሳ ከተሞች አካባቢ እንደሆነ ዘገባው አመልክቷል።

የዜና ወኪሉ በውርጌሳ አካባቢ የአውሮፕላን ድብደባ እንደነበር የዲፕሎቲክ ምንጮችም እንዳረጋገጡለት ነው የዘገበው።

በጉዳዩ ላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ክልልም ሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቃል አቀባዮች ያሉት ነገር የለም።

በሰሜን ዕዝ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የተጀመረው የሕወሃት ኃይሎች እና የፌዴራል መንግስቱ ጦርነት በቀጣዩ ጥቅምት ወር መጨረሻ አንድ ዓመት ይደፍናል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img