Sunday, July 7, 2024
spot_img

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ተደርገው ተሾሙ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 26፣ 2014 ― የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) መሪ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተቋቋመው አዲሱ ካቢኔ ውስጥ የትህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ ተሹመዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእጩነት ያቀረቧቸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበሩ አቶ በለጠ ሞላ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ተደርገዋል፡፡

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኦነግ አመራሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳን የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡ አቶ ቀጀላ መርዳሳ በኦነግ ሊቀመንበር አተቶ ዳውድ ኢባሳ ከገዢው ፓርቲ ብልጽግና ጋር ቅርበት አላቸው በሚል የሚከሰሱ ናቸው፡፡

በዛሬው የተወካዮች ምክር ቤት ውሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አቶ መላኩ አለበል የኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣ አቶ ገብረመስቀል ጫላ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስትር፣ አቶ ታከለ ኡማ በንቲ የማዕድን ሚንስትር፣ አምባሳደር ናሲሴ ጨሊ የቱሪዝም ሚንስትር፣ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የስራና ክህሎት ሚንስትር፣ አቶ አሕመድ ሽዴ የገንዘብ ሚንስትር፣ አቶ ላቀ አያሌው የገቢዎች ሚንስትር፣ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ አደላ የፕላንና ልማት ሚንስትር፣ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚንስትር፣ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ኢብራሂም የከተማና መሰረተ ልማት ሚንስትር፣ ዶ/ር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ የውሃና ኢነርጂ ሚንስትር፣ ኢ/ር አይሻ መሐመድ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚንስትር፣ ዶ/ር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር፣ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስትር፣ ዶ/ር ጌዲኦን ጢሞቲዎስ የፍትህ ሚኒስቴር ሚንስትር፣ አቶ ብናልፍ አንዷለም የሰላም ሚንስትር እና አቶ ኡመር ሁሴን የግብርና ሚንስትር እንዲሆኑ በእጩነት አቅርበው ጸድቆላቸዋል፡፡   

በዚህ የካቢኔ ሹመት የሕዳሴ ግድብን በተመለከቱ ጉዳዮ ከፍተኛ ተሳትፎ የነበራቸው የውሃና ኢነርጂ ሚንስትሩ ዶክተር ስለሺ በቀለ ሳይካተቱ ቀርተዋል፡፡

ዚሁ የካቢኔ ሹመት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለጥቂት ጊዜያት የመሩት ዶ/ር አብርሃም በላይ የመከላከያ ሚንስትር ተደርገው ተሹመዋል፡፡

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረቡ እጩዎችን በ2 ተቃውሞ እና በአስር ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ አጽቆታል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img