Monday, September 23, 2024
spot_img

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ተለቀቀ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 25፣ 2014 ― ባለፈው ቅዳሜ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ተነግሮ የነበረው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ መለቀቁ ተነግሯል፡፡

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ የሚመራው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ቅዳሜ መስከረም 22 በአዲስ አበባ ከተማ በተከበረው የእሬቻ በዐል ወቅት አንዳንድ ታዳሚዎች በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችን እንዲፈቱ ሲጠይቁ እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ላይ ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ የሚያሳይ ቪድዮ ለቆ ነበር፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ነበር የተነገረው፡፡

የጋዜጠኛውን እስር ተከትሎ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገቱት ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (ሲፒጄ) እና ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን መንግስት ጋዜጠኛውን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀው ነበር፡፡

የጋዜጠኛው እስር በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ በፌደራል ፖሊስ እጅ ስር እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ለምን በቁጥጥር ስር እንዳዋለው የተናገሩት ነገር አልነበረም፡፡

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ቅዳሜ እለት በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መኖሪያ ቤቱ ላይ ፍተሻ መካሄዱ ተነግሯል፡፡

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ አሁን ከሚሠራበት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ቀድሞ፣ በዶይቸ ቨለ ሲሠራ እንዲሁም ሥመ ጥር በነበረው አዲስ ነገር ጋዜጣ ከመስራቾቹ መካከል እንደነበር ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img