Monday, September 23, 2024
spot_img

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእስር እንዲለቀቅ ጠየቁ

 

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 25፣ 2014 ― ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገቱት ኮሚቲ ቱ ፕሮቴክት ጆርናሊስትስ (ሲፒጄ) እና ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ባለፈው ቅዳሜ መስከረም 22 በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ የተነገረው የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ መስራችና ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተስፋለም በኢትዮጵያ ኢንሳይደር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በኢሬቻ በዓል ላይ የተነሳውን ተቃውሞ ቪዲዮዎች ከለጠፈ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በቁጥጥር ስር መዋሉን ሲፒጄ ገልጿል።

ይህ ተግባር ‹‹መንግሥት በፕሬሱ ላይ ነጻ የሆነ ወይም የተቃውሞ ሽፋንን ከማበረታት ይልቅ ለማፈን የሚያደርገው ተከተታይ ጥቃቶችን የሚያጋልጥ ነው›› ነው ያለው ሲፒጄ፣ ፖሊስ ጋዜጠኛውን በአስቸኳይ እንዲፈታው ጠይቋል።

ሲፒጄ ጋዜጠኛው ከዚህ ቀደም በሽብር ወንጀል ከአንድ ዓመት በላይ መታሰሩን ድርጅቱ ያስታወሰ ሲሆን፣ ‹‹የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ወደቀደመው ሚዲያው አፈና ስልቶች መመለሱ የሚያሳዝን›› መሆኑንም ገልጧል፡፡  

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በበኩሉ በበዓሉ ላይ የተሰማውን ተቃውሞ ሲቀርጽ በቁጥጥር ስር የዋለው ተስፋለም በአስቸኳይ እንዲፈታ የመንግስት ባለስልጣናትን ጠይቋል። ‹‹በአገሪቱ ውሰጥ የፀረ መንግሥት ተቃዋሚዎችን መቅረጽ ክልክል ነው ወይ›› ሲል ጥያቄ የሰነዘረው ቡድኑ፣ ተስፋለምን ‹‹ከሥራው በስቀር ምንም አላደረገም። ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም›› ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል።

የጋዜጠኛው እስር በተመለከተ የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሊሳ አብዲሳ በፌደራል ፖሊስ እጅ ስር እንደሚገኝ ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ ፖሊስ ለምን በቁጥጥር ስር እንዳዋለው የተናገሩት ነገር የለም፡፡

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ቅዳሜ እለት በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መኖሪያ ቤቱ ላይ ፍተሻ መካሄዱ ተነግሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img