Sunday, November 24, 2024
spot_img

በኢትዮጵያውያን የሚመራ ብሔራዊ ውይይት ሊካሄድ መታቀዱን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 24፣ 2014 ― በዛሬው ዕለት ለቀጣይ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያን እንዲመሩ የተሰየሙት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ፣ በኢትዮጵያውያን የሚመራ ብሔራዊ ውይይት ሊካሄድ መታቀዱን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሔራዊ ውይይቱ “ችግሮቻችንን በጠረጴዛ ዙሪያ ይፈታሉ ብለው የሚያምኑትን” የሚያካትት እንደሚሆን ጠቁመዋል።

በዚህ የበዐለ ሲመት ንግግራቸው ትግራይ ጥቅምት 24፣ 2013 ተቀስቅሶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተዛመተው እና “በክህደት እና በእብሪት የተጠነሰሰ” ነው ያሉት ግጭት፣ “እንደ ሀገር እጅግ ከባድ ዋጋ” ማስከፈሉንም ገልጸዋል።

“ጠላት ብረት አንስቶ እንደ ብሌናችን የምናየውን የሰሜን እዝ አጠቃ፤ የጥሞና ጊዜ እንስጥ ባልንበት ጊዜም ሕጻናትን እያስታጠቀ በርካታ ዜጎቻችንን አጠቃ፤ ንብረትም አወደመ” ሲሉም ተደምጠዋል።

“እኛ ኢትዮጵያውያን ሰልፍ ይዘን ስንዘምትም ሆነ ሰይፍ ይዘን ስነነሳ ጠባችን ኢትዮጵያ ጠል ከሆኑት ጋር ብቻ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “ኢትዮጵያ የተማሏ አቅም እና አቋም ያለው የፀጥታ ኃይል ታደራጃለች” ሲሉም ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፥ “በመጪው ዘመን ብዝኃነታችንን በጌጥነት ተቀብለን መታረቅ የሚችል ሐሳባችንን አስታርቀን መከበር የሚገባው ልዩነቶቻችችን አክብረን ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠንክረን ወደ ከፍታ የምንተምበት ጊዜ ይሆናል” ያሉም ሲሆን፣ “ይህ እንዲሳካ የፖለቲካ ልዩነቶቻችንን ለማጥበብ አካታች ብሔራዊ የውይይት መድረክ እናካሂዳለን” ብለዋል።

በዛሬው ዕለት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የጠቅላ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዐለ ሲመት ላይ የጎረቤት አገራን ጨምሮ ሌሎችም የአፍሪካ አገራት መሪዎች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ከታደሙት መካከል የጎረቤት ኬንያ፣ የሶማሊያ እና የጁቡቲ መሪዎች ይገኛሉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img