Sunday, October 6, 2024
spot_img

የኢቢሲ የፌስቡክ ገጽ ሐክ መደረጉን ባልደረቦቹ አሳወቁ

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የፌስቡክ ገጽ ከደቂቃዎች በፊት ሐክ መደረጉን የጣቢያው ባልደረቦች አሳውቀዋል፡፡

የብሔራዊ ተቋሙ ሚዲያ ሐክ ተደርጓል በተባለበት ሰአት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕወሓት ጋር ድርድር እናደርጋለን የሚል መልእክት በዛሬው እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አድርጎታል በተባለ ‹‹የዝግ ስብሰባ›› ላይ መናገራቸውን የሚገልጽ ዜና ተጋርቷል፡፡

ዜናው አያይዞም ‹‹በትግራይ ሕዝብ ላይ ሰየደረሰው ግፍና መከራ በዓለም ፊት አዋርዶናል›› ማለታቸውም ሠፍሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ‹‹የኤርትራ ሠራዊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከሐገራችን ኢትዮጵያ እንዲወጣና በውስጣችን እየተስተዋሉ ያሉ ግጭቶች በኢትዮጵያ ባሕል መሠረት እንዲፈቱ›› ማለታቸውም ተገልጧል፡፡

የጣቢያው የፌስቡክ ገጽ ሐክ መደረጉን የተቋሙ ባልደረቦ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያመለከቱ፣ ከዚህ በኋላ የሚሠፍሩ መረጃዎች የድርጅቱ አለመሆናቸውን እወቁት ሲሉ አስፍረዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img