Sunday, November 24, 2024
spot_img

ወደ ፖርት ሱዳን የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ በሱዳን የሕክምና እና ነዳጅ አቅርቦት እየተሟጠጠ ነው ተባለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 24፣ 2014 ― በቤጃ ጎሳ አባላት ተቃውሞ ሰበብ ወደ ፖርት ሱዳን የሚወስደው መንገድ መንገድ በመዘጋቱ ሱዳን የሕክምና እና ነዳጅ እንዲሁም ስንዴ አቅርቦቷ እያተሟጠጠ መሆኑ ተነግሯል።

ከቀናት በፊት የቤጃ ጠቅላይ ም/ቤት ተብሎ የሚጠራው የቤጃ ጎሳ አባላት ተቆርቋሪ ያሰማውን ጥሪ ተከትሎ ዋናው መንገድ አምስት ቦታዎች በላይ መዘጋቱ ተዘግቦ ነበር፡፡ በተቃውሞው ወደ ፖርት ሱዳንና ሱዋኪን ወደቦች የሚወስደው መንገድ በሬድሲ ግዛት አቃባን ጨምሮ በሶስት ቦታዎች ላይ የተዘጋ ሲሆን፣ ከግብጽ ጋር የሚያገናኘው ኦሲፍ መንገድም በተቃውሞ መዘጋቱ ተገልጿል፡፡ ከሬድ ሲግዛት በተጨማሪ በከሰላ ግዛት በሁለት ቦታዎችና በገዳሪፍ ግዛት በሶስት ቦታዎች መዘጋቱም ነው የተዘገበው፡፡

ለቤጃ ጎሳ አባላት ተቃውሞ መነሻ ነው የተባለው አባላቱ የሚኖሩበት ግዛት ኋላ ቀር ነው የሚል መሆኑም ይነገራል፡፡

የፖርት ሱዳን ወደብ መዘጋቱን ይፋ ያደረገው የአገሪቱ ካቢኔ፣ ተቃውሞ አድራጊዎቹ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲያሰሙ የጠየቀ ሲሆን፣ አሁን እየወሰዱ የሚገኘው እርምጃ የመላው ሱዳንያውያንን ጥቅም የሚጎዳ ነው ብሎታል፡፡

ለተፈጠረው ችግ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንደሚፈልግለት ያሳወቀው ካቢኔው፣ ተቃውሞ አድራጊዎቹ ከመንግስት ጋር ለንግግር እንዲቀመጡም ነው ጥሪ ያቀረበው፡፡  

ከሁለት ሳምንታት በፊት መፈንቅለ መንግስት ተሞክሮ ከሽፎባታል በተባለችው ሱዳን፣ አገሪቱን የሚመሩት የሲቪልና ወታደራዊ አመራሮች ሲካሰሱ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የሲቪል አስተዳድሩ ‹‹ወታደራዊ አመራሩ ወደ ዴሞክራሲ የሚደረገውን ሽግግር እያደናቀፈ ነው›› በሚል የሽግግር ምክር ቤት መሪው ዐብዱልፈታህ አል ቡርሃን የሚመሩትን ጦር የወነጀለ ሲሆን፣ ‹‹የሰቪል አስተዳድር ፖለቲከኞች ለመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ምክንያት ናቸው›› ብለው ነበር፡፡

ምከትል አዛዡ አሕመት ዳጋሉ በበኩላቸው ‹‹ፖለቲከኞች የሱዳን ጦር አምባገነኑን የአልበሽር ስርዓት በመገርሰስ የከፈለውን መስዋዕት ረስተው ጦሩን ማናናቃቸው መፈንቅለ መንግስት እንዲፈጸም በር ከፍተዋል›› ሲሉ የሲቪል አስተዳድሩን ተችተዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img