Friday, November 22, 2024
spot_img

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ታወቀ

የኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ታውቋል።

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከቅዳሜ መስከረም 22፣ 2014 ፈፋድ ጀምሮ ያለበትን እንደማያውቁ ወዳጆቹ ማሳወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሊሳ ዐብዲሳ ነግረውኛል ብሎ ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው ጋዜጠኛ ተስፋዓለም ወልደየስ በአሁኑ ወቅት በፌደራል ፖሊስ እጅ ስር ይገኛል።

ኃላፊው ተስፋዓለም በአሁኑ ጊዜ “የፌደራል ፖሊስ የምርመራ ቢሮ የሜክሲኮ ማቆያ እንደሚገኝ” ገልጸው፤ “ምንም የሚፈጠር ነገር የለም። ያለውን ነገር እያጣራን ነው። ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም” ሲሉ መናገራቸው ተመላክቷል።

የወንጀል ምርመራ ቢሮ ምክትል ኃላፊው፤ ጋዜጠኛ ተስፋዓለም በምን ወንጀል ተጠርጥሮ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል ነው የተባለው።

ጋዜጠኛው የሚመራው ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ቅዳሜ እለት በእሬቻ በዐል ወቅት አንዳንድ ታዳሚዎች በእስር ላይ የሚገኙ ፖለቲከኞችን እንዲፈቱ ሲጠይቁ እንዲሁም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ላይ ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ የሚያሳይ ቪድዮ ለቆ ነበር።

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ አሁን ከሚሠራበት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ቀድሞ፣ በዶይቸ ቨለ ሲሠራ እንዲሁም ሥመ ጥር በነበረው አዲስ ነገር ጋዜጣ ከመስራቾቹ መካከል እንደነበር ይታወቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img