Tuesday, October 8, 2024
spot_img

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ የመስቀል በዓል ላይ ሦስት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ጊዳ አያና ወረዳ አንገር ጉትን መንደር አራት ቀበሌ፣ ሦስት ንጹኃን ዜጎች የመስቀል በዓል ላይ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን ነዋሪዎቹ ነግረውኛል ብሎ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስነብቧል፡፡

እንደ ነዋሪዎቹ ከሆነ ታጣቂዎቹ ግድያውን የፈጸሙት የተፈጸመባቸው መስቀል በዓልን ለማክበር የተዘጋጀው የደመራ በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሦስት ሰዎች ናቸው፡፡

ግድያው የተፈጸመባቸው ንጹኃን ገበሬዎች ናቸው የሚሉት ነዋሪዎቹ፣ የሟቾቹን ሬሳ አንስተው ለመቅበር ታጣቂዎቹ ስለከለከሏቸው በዕለቱ መቅበር እንዳልቻሉ ተናግረዋል። በመጨረሻ ከአንገር ጉተን በመጡ የመከላከያ ኃይሎች እርዳታ በማግስቱ እንደተቀበሩ ነው የገለጹት።

ነዋሪዎቹ አያይዘውም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት እና ኦነግ ሸኔ በመተባበር ከነሐሴ መጨረሻ ጀምሮ በምሥራቅ ወለጋ ዞን በየዕለቱ ሰዎች እየገደሉ ነው ብለዋል።

ጋዜጣው ከሳምንት በፊት ታጣቂ ኃይሎቹ በኪራሙ ወረዳ ቃና ውልማይ ቀበሌ በሰነዘሩት ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎችን መግደላቸውን አያይዞ ዘግቧል፡፡

‹‹ዜጎች የሚገደሉትም አካባቢያችንን ለቃችሁ ወደ ክልላችሁ ሒዱ›› በሚል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img