Sunday, November 24, 2024
spot_img

አንዲት እናት ላይ በልጇ ፊት ድብደባ የፈጸሙ ሁለት ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰላም ሚኒስትሯ አስታወቁ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 22፣ 2014 ― አንዲት እናት ላይ በልጇ ፊት ድብደባ የፈጸሙ ሁለት ፖሊሶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል አስታውቀዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በጀሞ ሚካኤል አካባቢ ሁለት የፖሊስ አባላት አንዲት እናትን በልጇ ፊት ዘግናኝ ድብደባ ሲፈጽሙባት የሚያሳየው ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር መድረኮች መሰራጨቱን ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፡፡

የሰላም ሚኒስትሯ ልብ የሚሰብር ሲሉ የገለጹት ሲሆን፣ የተጀመረው ‹‹ተቋማዊ ለውጥ ሀላፊነትን ከነተጠያቂነቱ አጣምሮ የያዘ›› መሆኑን በማስታወስ፣ በጉዳዩ ላይ ከፌዴራል ፓሊስ አመራሮች ጋር መረጃ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለት የፓሊስ አባላት ላይ ‹‹ሕጉን ተከትሎ የማጣራትና ተገቢው የእርምት እርምጃ› እንደሚወሰድም አመልክተዋል፡፡  

ወይዘሮ ሙፈሪሃት አያይዘውም ‹‹ዜጎች ለሰብዓዊ መብት መከበር እንዲህ አይነት ህገ ወጥ ተግባራትን በመከታተልና በማጋለጥ ረገድ ማህበራዊ ሚዲያን አዎንታዊ ለሆነ ተግባር ማዋል መቻላቸው ተጠናክሮ ሊቀጥል›› እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡  

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img