Friday, November 22, 2024
spot_img

በአዲስ አበባው የኢሬቻ በዓል አከባበር የተቃውሞ ድምጾች ተሰሙ

 

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እየተከበረ በሚገኘው የኢሬቻ በዓል አከባበር የተቃውሞ ድምጾች ተሰምተዋል፡፡

በዚሁ የበዐል አከባበር ላይ ከተሰሙት የተቃውሞ ድምጾች መካከል በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባሉ አቶ ጃዋር መሐመድ እንዲፈቱ የሚጠይቁ ይገኙበታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ላይ ተቃውሞዎች ሲስተጋቡ የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችም በማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ ተጋርተዋል፡፡

በዛሬው እለት በደማቅ ሁኔታ በአዲስ አበባ እየተከበረ የሚገኘው የእሬቻ በዐል፣ በነገው እለት ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዴ የሚከበር ይሆናል፡፡

በቅርብ ዐመታት ፖለቲካዊ የተቃሞ ድምጾችም በሚያስተናግደው በዚሁ በዐል፣ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የቱለማ አባገዳ የእሬቻ አከባበር አስተባባሪ አባ ገዳ ጎበና ሆላ ለሚዲያዎች ተናግረው ነበር፡፡

አባ ገዳ ጎበና ሆላ በዘንድሮው የኢሬቻ በዐል ‹‹ሳር ብቻ ይዘን ነው ወደ ወንዝ የምንወርደው፤ ፖለቲካው ለሌላ ጊዜ ይቆየን›› ማለታቸውን ቢቢሲ አስነብቦ ነበር፡፡

ከማለዳ ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ የሚገኘው በዐል ታዳሚዎች በተለያዩ አልባሳት ደምቀው ታይተዋል፡፡

 

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img