Monday, September 23, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም በአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አመራር ዘርፍ ተሸለሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወልደ ገብረማርያም ፍላይት ግሎባል መስከረም 17 በለንደን ባዘጋጀው የአየር መንገዶች የቢዝነስ ስትራቴጂ ሽልማት ላይ “በአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አመራር” ዘርፍ ተሸላሚ ሆነዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ላደረጉት የሚመሰገን የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አመራር ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመወከል የተሸለሙት።

ሽልማቱ በኮቪድ 19 ቀውስ ወቅት በዋና ሥራ አስፈፃሚው በኩል የተሰጡ የአየር መንገዱ ቀልጣፋ ስልቶችና የችግር አመራሮችን ዕውቅና ለመስጠት የተዘጋጀ ነው።

የንግድ ሥራ አፈፃፀም፣ የአውታረ መረብ ስትራቴጂና በችግሩ ጊዜ ያለው የፈጠራ አስተሳሰብ ለሽልማቱ ቁልፍ ከሆኑት መስፈርቶች መካከል ይገኙበታል።

ሽልማቱን በተመለከተ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ፍላይት ግሎባል እና የአየር መንገዶች የቢዝነስ ስትራቴጂ ሽልማት ዳኛ ፓነል የእኛን ልዩ የችግር አያያዝ ችሎታዎች፣ ቅልጥፍናን፣ የውሳኔ አሰጣጥን ፍጥነት፣ የፈጠራ ችሎታን እና የመቋቋም አቅማችንን አይተው ይህን ሽልማት በማግኘቴ በጣም ተደስቻለሁ” ያሉ ሲሆን፤ በአጠቃላይ በዓለም ላይ የተከሰተው ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ግዙፍነት እና ውድመት ቢኖረውም በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ቀውሱን በተሳካ ሁኔታ ወደ ዕድል መቀየሩን ተናግረዋል።

አክለውም “ለሁሉም የኢትዮጵያ ማኔጅመንት ቡድን አባላት፣ ለዳይሬክተሮች ቦርድ እና ለ17 ሺህ ታታሪ ሠራተኞች በጣም አመሰግናለሁ። የአየር መንገዶች የቢዝነስ ስትራቴጂ ሽልማት እና ለፍላይት ግሎባል ለሽልማት ስለመረጡኝ ማመስገንም እፈልጋለሁ።” ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም ዙሪያ አስፈላጊ የህክምና አቅርቦቶችን በማመላለስ ውጤታማነቱ እንደ የአለም የምግብ ፕሮግራም ያሉ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እውቅና ሰጥተውታል።

አየር መንገዱ ከ50 ሚሊዮን በላይ የኮቪድ 19 ክትባቶችን ለተለያዩ አገሮች በማሰራጨትና የሰብአዊ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ባደረገው ሚና አድናቆት አግኝቷል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img