Friday, November 22, 2024
spot_img

የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ሊወያይ ነው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ጉዳይ ላይ እንደሚወያይ ተገልጧል፡፡

የምክር ቤቱ መርሃ ግብር እንዳመለከተው ቀደም ሲል ከተያዘ ጉዳይ ውጪ በሆነ መድረክ የፀጥታው ምክር ቤት አባልት በትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ ይወያያሉ ብሏል።

ይህ የምክር ቤቱ ስብሰባ መንግሥት በትላንትነው እለት ሰባት የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንደገቡ ገልጾ፣ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ ካዘዘ በኋላ የሚደረግ የመጀመሪያው ስብሰባ ነው።

ዛሬ ይካሄዳል የተባለውን ይህን የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንዲካሄድ የጠየቁት የምክር ቤቱ አባል የሆኑት ኢስቶኒያ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዩክሬንና አሜሪካ ናቸው።

አስራ አምስት አባላት ያሉት ከፍተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የውሳኔ አካል የሆነውን የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤትን የፕሬዝዳንትነት መንበር ዛሬ በሚጀምረው የፈረንጆቹ የጥቅምት ወር የምትረከበው ኬንያ ትሆናለች፡፡

ምክር ቤቱ ለዛሬ በያዘው ስብሰባው በጥቅሉ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ እንደሚወያይ የተነገረ ሲሆን፤ ትላንት መንግሥት የተመድ ሠራተኞችን ከአገሩ እንዲወጡ የሰጠው ውሳኔ ላይ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።

በተጨማሪም በሠሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ የትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትንና ያለውን አሳሳቢ ሰብአዊ ቀውስ በተመለከተ ሊወያይ ይችላል ተብሏል።

የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በትግራይ ጉዳይ ላይ ብቻ ለስምንት ጊዜያት ስብሰባ አካሂዷል። ምክር ቤቱ በትግራይ ያለውን ቀውስ በተመለከተ ለመጨረሻ ጊዜ ስብሰባ የተቀመጠው ባለፈው ነሐሴ ወር መጨረሻ ነበር፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img