Friday, November 29, 2024
spot_img

የሂውማን ራይትስ ዋች ኃላፊዋ የዶ/ር ዳንኤል በቀለን ሽልማት ተቃወሙ

አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― የሂውማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሺያ ባደር የጀርመን አፍሪካ ፋውንዴሽን (ዲኤኤስ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለን (ዶ/ር) ለመሸለም መወሰኑ “ወቅቱን ያልጠበቀ እንዲሁም የተሳሳተ መልዕክት የሚያስተላልፍ” ነው ሲሉ ወቀሱ።

የላቲሽያ ባደር ተቃውሞ የመጣው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸ በኋላ ነው፡፡

ላቴሺያ አስተያየቱን የሰጡት በሚቀጥለው ሳምንት የሚመሰረተው አዲሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ብሎም በዕለቱ የሚታደሙት የአፍሪካ መሪዎች ላይ በትግራይ ክልል ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በተመለከተ ጫና ለማሳደር በተጠራው የፕሬስ መግለጫ ላይ ነው።

“አሁን ባለንበት ሰዓት፤ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ክብደትን ከግምት ውስጥ ከከተትን፤ ምንም እንኳን አንድ ሰው ለሰብአዊ መብቶች ያለው የቁርጠኝነት የኋላ ታሪክ የተመሰከረለት ቢሆንም እንዲህ ያለ ሽልማት መስጠት የተሳሳተ ዲፕሎማሲያዊ መልዕክት ያስተላልፋል” ሲሉ ላቴሺያ ተናግረዋል።

ኃላፊዋ አክለውም “የእነዚህ ጥሰቶች ሰለባዎች ብሎም ከጥቃቶቹ የተረፉት ሰዎች እነዚህን የፌደራል ተቋማት አያምኗቸውም። ይህ ባለፈው አመት በኦሮሚያ የሰራነውን ጥናት ጨምሮ በዚህ ዓመት በሰራናቸው ጥናቶች እንዲሁም በትግራይ ክልል ካሉ የጥቃቶቹ ሰላባዎች የተረዳነው በፌደራል ተቋማት ላይ ዕምነት እንደሌላቸው ነው” ብለዋል።

“ጀርመን በዚህ ሰአት ለአንድ የፌደራል ተቋም መሪ እንዲህ ያለ ሽልማት ለመስጠት መወሰኗ የተሳሳተ መልክት የሚያስተላልፍ ይሆናል” ሲሉ የቀድሞ የተቋማቸው ከፍተኛ አመራር የነበሩትን የዶ/ር ዳንኤልን መሸለም ተቃውመዋል።

ከ30 ዕጩዎች መካከል በሙሉ ድምፅ የተመረጡት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፣ ሽልማታቸውን በኅዳር ወር እንደሚቀበሉ ይጠበቃል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img