አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― ለዛሬ እንዲካሄድ ቀን ተቆርጦለት የነበረው ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የአፋር ክልላዊ መንግሥት ምስረታ አለመካሄዱ ተነግሯል፡፡
በክልሉ መንግስት ምስረታ ላይ ለጉባኤው በተደረገው ጥሪ መሰረት አዳዲስና ነባሮቹ አባላት ወደ አዳራሹ ገብተው የነበረ ቢሆንም፣ ጉባኤው ሳይካሄድ መቅረቱን የሚያመለክቱ መረጃዎች ጥተዋል፡፡
በጧቱ ክፍለ ጊዜ ሳይካሄድ የቀረው ጉባኤ፣ ከምሳ በኋላ ቢጠበቅም አለመደረጉ የተነገረ ሲሆን፣ ጉባኤውን ለመታደም በአዳራሽ የተገኙ ሰዎች ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ጉባኤው ላለመካሄዱ እስካሁን ድራስ ይፋ ያደረገው መረጃ የለም፡፡