አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― ጎረቤት አገር ሱዳን በ24 ሰአት ውስጥ 4 ሺሕ ኢትዮጵያውያን ወደ አገሯ መዝለቃቸውን ገልጻለች፡፡
አል ዐይን ዐረቢኛው የተጠቀሱት ኢትዮጵያውያን ስደተኞ ከጉሙዝ እና ቅማንት አካባቢ መሆናቸውን ዘግቧል፡፡
ማእሙን አልደው ዐብዱረሂም የተባሉ የባሰንዳ አካባቢ አስተዳዳሪ የስተደተኞቹ ወደ ሥፍራው መዝለቃቸውን ተከትሎ የሰብዓዊ እገዛ ማድረግ አስቸኳይ መሆኑን በመግለፅ፣ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል፡፡
ሱዳን በጥቅምት ወር የተቀሰቀሰውን የትግራይ ጦርነት ተከትሎ ከክልሉ እና አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም ከሌሎችም የኢትዮጵያ አካባቢዎች 75 ሺሕ ያህል ሰዎችን በስደተኝነት ማስተናገዷን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡