አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― የአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር መስራች ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
ዛሬ ጧት በጀመረው የምክር ቤቱ ጉባዔ ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬን አፈ ጉባዔ አድርጎ ሲመርጥ፣ አቶ አማረ ሠጤን ደግሞ ም/አፈ ጉባኤ ተደርገው ተመርጠዋል።
ምክር ቤቱ በቀጣም ውሎው የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር እና ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ይሰይማል። በተጨማሪም የካቢኔ ሹመቶች ቀርበው በምክር ቤቱ ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።