አምባ ዲጂታል፣ ሐሙስ መስከረም 20፣ 2014 ― የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በክልልነት የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጠት በቦንጋ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።
በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ በወሰዱባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፅ እየሰጡ ይገኛሉ። የድምፅ የመስጠት ሂደቱም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ነው እየተካሄደ እንደሚገኝ ኢዜአ መታዘቡን ዘግቧል።
የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች-ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ኮንታ ልዩ ወረዳ “በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል” ለመደራጀት የሚያካሂዱት ሕዝበ ውሳኔ ሲሆን፣ ለዚህ ሕዝበ ውሳኔ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።