Sunday, October 6, 2024
spot_img

ሁለት የሲዳማ ክልል የፓርላማ ተመራጮች ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ላይገቡ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 19፣ 2014 ― በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሲዳማ ክልል ለፓርላማ የተወዳደሩ ሁለት ተመራጮች፤ በመጪው ሳምንት መጀመሪያ ወደሚከፈተው የተወካዮች ምክር ቤት ላይገቡ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) አመራሮች የሆኑት ሁለቱ ግለሰቦች፤ በፓርቲያቸው እና በሲዳማ ብልጽግና መካከል ያለው የቅንጅት ሂደት እልባት ካላገኘ ወደ ፓርላማ ላለመግባት መወሰናቸውን እንደነገሩት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር አስነብቧል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ከመቀላቀላቸው በፊት ያስቀመጡት ቅድመ ሁኔታ እንዲሟላ የጠየቁት የፓርላማ ተመራጮች፤ አቶ ሰላሙ ቡላዶ እና አቶ ደሳለኝ ሜሳ ናቸው። የሲአን ኢኮኖሚ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰላሙ በሲዳማ ክልል በቡርሳ ምርጫ ክልል ተወዳድረው ያሸንፉ ሲሆን፤ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ደሳለኝ ደግሞ በቱላ ምርጫ ክልል ለፓርላማ የተመረጡ ናቸው።

ሁለቱ ተመራጮች ባለፈው ሰኔ ወር በተካሄደው ምርጫ ለውድድር የቀረቡት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው እንደነበር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያሳያል። ሁለቱ የሲአን ከፍተኛ አመራሮች በብልጽግና ስም ለምርጫ የቀረቡት፤ ፓርቲያቸው ከሲዳማ ብልጽግና ፓርቲ ጋር የፈጠረው ቅንጅት “በፍጥነት ዕውቅና ያገኛል” ብለው በማሰባቸው እንደነበር ያስረዳሉ።

የፓርላማ ተመራጮቹ ከቅንጅቱ ጋር በተያያዘ ያስቀመጧቸው ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ካልተሟሉ፤ በሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ የሚመሰረተው የፌደራል መንግስት ፓርላማ አካል እንደማይሆኑ ማስታወቃቸውን ዘገባው አክሏል።

የፎቶ ምንጭ፡ ኢትዮጵያን ኢንሳይደር

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img