Tuesday, December 3, 2024
spot_img

የንግድ ተቋማት የሚገጥማቸው የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ እንዲካካስ ተወሰነ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 19፣ 2014 ― የንግድ ተቋማት በውጭ ገንዘብ ከፈጸሙት ግብይት ወይም የንግድ እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ የሚገጥማቸው የምንዛሪ ኪሳራ እንዲካካስ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባካሄደው ስብሰባው፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የገቢ ግብር ደንብ ላይ ተስተውለዋል ተብለው የተለዩ የሕግ ክፍተቶች ላይ በመወያያት የማሻሻያ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ከለተዩት ክፍተቶች መካከል አንዱም የንግድ ተቋማት በውጭ አገር ገንዘብ ግብይት ከፈጸሙ በኋላ በሚፈጠር የውጭ ምንዛሪ ምጣኔ ልዩነት፣ የሚደርስባቸውን የምንዛሪ ኪሳራ ማካካስ የሚችሉበት የሕግ አግባብ አለመኖሩና በዚህ የተነሳ በንግድ ተቋማቱ ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ነው።

እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ከባንኮች ውጪ ያሉ ሌሎች የንግድ ሥራ ድርጅቶች ለካፒታል ንብረት ማፍሪያ የወሰዱትን ብድር በሚከፍሉበት፣ ወይም በውጭ ምንዛሪ ሌሎች የንግድ ሥራ እንቅስቃሴዎችን በሚያከናውኑበት ጊዜ የውጭ ምንዛሪ ኪሳራ ያጋጥማቸዋል።

በዚሁ መሠረት በሥራ ላይ የሚገኘው የገቢ ግብር ደንብ በውጭ ምንዛሬ ግብይት የደረሰ ኪሳራ እንዲካካስ የሚፈቅደው፣ በውጭ ምንዛሪ ግብይት ለተገኘ ጥቅም ብቻ ነው።

ነገር ግን የንግድ ተቋማት ለካፒታል ንብረት ማፍሪያ የወሰዱትን ብድር በሚከፍሉበት ወቅት ወይም ሌላ ግብይት በውጭ ምንዛሪ ሲፈጽሙ፣ በምንዛሪ ለውጥ የሚደርስባቸው ኪሳራ ታሳቢ የሚደረግበት አሠራር አልነበረም።

እነዚህ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሪ የማይዙ በመሆኑ ከግብይቱ የሚያገኙት ጥቅም ስለሌለ፣ ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ ቆይተዋል።

በመሆኑም ይህን የሕግ ክፍተት ለማስተካከል በገቢ ግብር ደንብ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ተጠይቆ፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጉዳዩን ገምግሞ ማሻሻያው እንዲደረግ መወሰኑ ነው የተነገረው።

በተፈቀደው ማሻሻያ መሠረት በውጭ ምንዛሪ ግብይት ላይ ያጋጠመ ኪሳራ በሁለት ተከፍሎ ማካካሻ እንዲደረግበት ተወስኗል።

በዚህም መሠረት የውጭ ምንዛሪ ግብይቱ የተፈጸመው ከካፒታል ንብረት ግዥ ጋር በተያያዘ ከሆነ፣ የውጭ ምንዛሪ ኪሳራው የካፒታል ንብረቱ የተገዛበት ዋጋ ላይ ተደምሮ ለእርጅና ቅናሽ መሠረት እንዲሆን የሚፈቅድ ማሻሻያ በደንቡ ላይ እንዲደረግ ተፈቅዷል።

በሌላ በኩል የውጭ ምንዛሪ ግብይቱ የተፈጸመው ከካፒታል ንብረት ግዥ ጋር ባልተያያዘ ከሆነ፣ የውጭ ምንዛሪ ኪሳራው በግብር ዘመኑ እንደ ወጪ እንዲያዝ የሚፈቅድ ማሻሻያ እንዲደረግ ተወስኗል።

ሌላኛው በገቢ ግብር ደንቡ ላይ የታየው የሕግ ክፍተትና ማሻሻያ እንዲደረግበት የተጠየቀው ጉዳይ፣ ከካፒታል ዋጋ ዕድገት ጥቅም ላይ ከሚጣለው ግብር ጋር የተያያዘ ነው።

ለንግድ ሥራ የሚያገለግልን ሕንፃ ወይም አክሲዮን በሽያጭ በማስተላለፍ በሚገኝ የዋጋ ዕድገት ጥቅም ላይ የሚከፈለው የካፒታል ዋጋ ዕድገት ግብር አጣጣልን በተመለከተ የሚደነግገው የገቢ ግብር ደንብ፣ ሕንፃን በመሸጥ በሚገኝ የዋጋ (የካፒታል) ዕድገት ላይ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያ ወይም ቅናሽ ተደርጎ በሚገኘው ዋጋ ላይ ግብር እንዲከፈል ሲፈቅድ፣ ከአክሲዮን ሽያጭ በሚገኝ የዋጋ ዕድገት ጥቅም ላይ የዋጋ ግሽበት ማስተካከያን አለመፍቀዱ ግብር ከፋዮች በእኩል እንዳይስተናገዱ አድርጓል ነው የተባለው።

በመሆኑም ይህን ችግር ለማስተካከል ማሻሻያ ድንጋጌ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ተቀባይነት አግኝቷል።

አክሲዮን የሚሸጡ ግብር ከፋዮች የአክሲዮን ሰነዱ ሲወጣ በተቆረጠለት ዋጋ፣ ወይም አክሲዮን ሰነዱ ላይ በተጻፈው ዋጋ (Par Value) እና በተሸጠበ

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img