Sunday, October 6, 2024
spot_img

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሱዳን በውስጥ ችግሯ የውጭ ጣልቃ ገብነት መፍቀድ የለባትም አሉ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 18፣ 2014 ― ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሱዳን አሁን ባጋጠማት የውስጥ ችግሯ ላይ በግልጽ ወይም በድብቅ የሚደረግ የውጭ ጣልቃ ገብነትን መፍቀድ የለባትም ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

ከሰሞኑ በሱዳን ምስራቃዊ ክፍል በተነሳ ተቃውሞ ምክንያት ሀገሪቱ የጸጥታ ችግር ውስጥ ትገኛለች፡፡

በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ክስተት በጎ በሆነ መልኩና በወንድማዊነት እየተከታተሉት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ የውጭ ኃይሎች ‹‹ውስጣዊ ግጭት ውስጥ ስንገባ ወይም የኢኮኖሚ ቀውስ ሲያጋጥመን፤ የእነዚህን ኃይች የማጥቃት ፍላጎት ሲበዛ እናያለን›› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ኃይሎች ሉአላዊነታችንን በመጣስ ፍላጎታቸውን ለመጫንና ለመጥቃት ጉጉት እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡

ሱዳን ያጋጠማት ችግር በራሷ ጥበብ እንድትፈታው የተመኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ሱዳን ያለ ውጭ ጣልቃ ገብት በራሷ ተቋማት ‹‹ለውስጣዊ ችግሯ ውስጣዊ መፍትሄ እንደምታገኝ ተስፋ አለን›› ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህን መልእክት ባሰፈሩበት ጊዜ በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል የድንብር ውጥረት መስፈኑ ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img