በኢትዮጵያ የጋዜጠኝነት ሙያ እድገት ላይ አሻራውን ያሳረፈው አንጋፋው ጋዜጠኛ ከበደ አኒሳ ማረፉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማህበር አሳውቋል፡፡
‹‹የኢትዮጵያ ድምጽ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ከበደ አኒሳ፣ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዝደንት ሆኖ አገልግሏል፡፡ በተጨማሪም በወሎ የተከሰተውን ረሃብ ለቢቢሲው ጋዜጠኛ ጆናታን ድምቢልቢ ማሳየቱም ይጠቀስለታል፡፡