Thursday, December 5, 2024
spot_img

ጦርነቱ ከቀጠለ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ፕሮጀክቶች ብቻ ትኩረት እንደሚደረግ መንግሥት አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 17፣ 2014 ― በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአሸባሪነት ከተሰየመው ከሕወሓት ታጣቂዎች ጋር እየተካሄደ ያለው ጦርነት በዚሁ ከቀጠለ፣ በመልማት ላይ ካሉና ወደ ሥራ ይገባሉ ተብለው ከተያዙ አገራዊ ፕሮጀክቶች ውስጥ ቅድሚያ ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ላይ እንደሚያተኩር የፌዴራል መንግሥት አስታውቋል፡፡

በጦርነቱ በትግራይ፣ በአማራና በአፋር ክልሎች በደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ የፌደራል መንግሥት በርካታ ቢሊዮን ብሮች በሚቆጠር ሀብት ዕርዳታ እያቀረበ መሆኑን፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ሰሞኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

የፌደራል መንግሥት የተናጠል ተኩስ በማቆም ከትግራይ ክልል ከመውጣቱ አስቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለፓርላማው ባቀረቡት ሪፖርት ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውቀው ነበር፡፡

ይሁን አንጂ በቀጠለው ጦርነት እየደረሰ ባለው ቀውስ ምክንያት፣ የተቋረጡ ወይም የተስተጓጎሉ አገራዊ ፕሮጀክቶች ስለመኖራቸው የተጠየቁት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በጦርነቱ ምክንያት እስካሁን የፕሮጀክቶች ገንዘብ መጠን እየተቀነሰ ሲለቀቅ የነበረ ቢሆንም፣ የተቋረጡ ፕሮጅክቶች የሉም ብለዋል፡፡

‹‹ነገር ግን የሰብዓዊ ቀውሱ ወጪ አሁን ባለው ሁኔታ እየጨመረ ከመጣ፣ የሰዎችን ሕይወት ማዳን ቅድሚያ ስለሚሰጠው ትንሽ ከመንገድ፣ ትንሽ ከመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ብንቀንስ ትክክለኛ አካሄድ ይሆናል›› ብለዋል፡፡

በመሆኑም ወጪ እየጨመረ ከመጣና በተፈለገው መጠን ከአጋሮች የሚገኘው ሀብት ከቀነሰ፣ መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ፕሮክቶች ላይ የማተኮር አማራጭ ውስጥ ለመግባት እንደሚገደድ ተናግረዋል፡፡

የጦርነት ጉዳት አላስፈላጊ በመሆኑ ጦርነቱ ካሸነፍን በኋላ፣ በዚህች አገር ሁለተኛ ጦርነት እንዳይፈጠር አድርገን መሥራት ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በርካታ አገራዊ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የመንገድ፣ የአሌክትሪክ ኃይል፣ የመስኖ፣ የባቡር መስመሮች፣ ዝርጋታና የመሳሰሉት እያካሄደች ትገኛለች፡፡ በመገንባት ላይ ያሉ፣ ይገነባሉ ተብለው በዕቅድ የተያዙና የሀብት ድልድል ለወጣላቸው የመንገድ ፕሮጅክቶች ዋጋ ብቻ ከግማሽ ትሪሊዮን በላይ ብር እንደሚያስፈልጋት መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በፌደራል መንግሥት የሀብት ቋት ከሚገነቡት ፕሮጀክቶች ውጪ የበርካታ ፕሮጅክቶች ማከናወኛ የሀብት ምንጭ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ከግል፣ እንዲሁም ከአበዳሪዎችና ከዕርዳታ ምንጮች ቢሆንም አንዳንዶቹ ቃል የገቡትን ገንዘብ ለመልቀቅ ወደኋላ እያፈገፈጉና እያጉረመረሙ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img