Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሱዳን መንግሥት በድንበር አካባቢ የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥቃት ሰንዝረውብኛል አለ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 17፣ 2014 ― የሱዳን መንግሥት የኢትዮጵያ ወታደሮች በአዋሳኝ ድንበር ላይ ጥቃት ሰንዝረውብኛል ሲል ከሷል።

የአገሪቱ ጦር ባወጣው መግለጫ ኡማ ናራኪት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከኢትዮጵያ በኩል ተሰንዝሮብኛል ያለውን ጥቃት መመከቱን አስታውቋል።

እንደ ሱዳን ጦር አዛዥ ጀነራል ዐብደልፈታህ አል ቡርሃን ከሆነ ከኢትዮጵያ በኩል ጥቃት ተሰንዝሯል የተባለው ቅዳሜ ዕለት ነበር።

በቅርቡ በሱዳን ተከስቶ ከሸፈ የተባለውን መፈንቅለ መንግሥት ያስታወሱት አል ቡርሃን፣ ክስተቱ ጦሩ ሱዳንን እየጠበቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

ሬውተርስ በጉዳዩ ላይ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት በይፋ ምላሽ ባይሰጥም፣ አልጀዚራ ግን የመንግስት ባለስልጣናትን በመጥቀስ እንደዘገበው በሱዳን ድንበር አካባቢ የኢትዮጵያ ጦር ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረገም፤ የተባለው ጥቃትም አልተፈጸምም።

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር የተከሰተው ውጥረት ካገረሸ አስር ወራት ያህል ሲያስቆጥር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሰሞኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር መንግሥት በሁለቱ አገራት መካከል በድንበር ይገባኛል የተከሰተውን አለመግባባት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img