Saturday, September 21, 2024
spot_img

የኢትዮጵያ የውጭ ብድር የመክፈል አቅም ደረጃ ዝቅ ተደረገ

አምባ ዲጂታል፣ እሑድ መስከረም 16፣ 2014 ― የኢትዮጵያ የውጭ ብድር የመክፈል አቅም ደረጃው ዝቅ ያደረገው “ኤስ ኤንድ ፒ” የተባለው ዓለም አቀፍ የሀገራት ብድር ከፋይነት ደረጃ አውጭ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ይፋ ባደረገው የሀገራት ብድር ከፋይነት ደረጃ የኢትዮጵያን የውጭ ብድር የመክፈል አቅም ከደረጃ B- ወደ ደረጃ CCC+ ዝቅ እንዳደረገው ሬውተርስ ዘግቧል።

ድርጅቱ የኢትዮጵያን የውጭ ብድር የመክፈል ደረጃ ዝቅ ያደረገው፣ የገጠማትን ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እና የውጭ ዕዳ መክፈያ ጊዜ ሽግሽግ መዘግየቱን እንደ ምክንያት በመጥቀስ ነው።

ድርጅቱ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት የሀገሪቱን በጀት ጉድለት የሚሸፍነው በዋናነት የውስጥ ምርት እንደሚሆን ገልጿል።

ኤስ ኤንድ ፒ መንግስታት ብድር የመመለስ አቅማቸውን እየመዘኑ ደረጃ ከሚሰጡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተጠቃሽ ነው። ድርጅቱ የአገራትን አቅም እንደ ጥንካሬው ከAAA እስከ D ደረጃ የሚሰጥ ነው።

ድርጅቱ በሚያወጣው ደረጃ የአገራት አቅም በወረደ ቁጥር ብድር የማግኘት እድላቸው እየጠጠ እንደሚመጣና ብድሩን የሚያገኙ ከሆነም በከፍተኛ ወለድ እንደሚሆን የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img