Wednesday, December 4, 2024
spot_img

በኦፌኮ አመራሮች መካከል ክፍፍል ተፈጥሯል የተባለው መረጃ ሐሰት ነው ሲሉ የፓርቲው ዋና ጸሐፊ ተናገሩ

አምባ ዲጂታል፣ ቅዳሜ መስከረም 15፣ 2014 ― በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራሮች መካከል ክፍፍል ተፈጥሯል የተባለው መረጃ ሐሰት ነው ሲሉ የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለሸገር ተናግረዋል።

እንደ ዋና ጸሐፊው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በፓርቲው አመራሮች መካከል በዓላማ ደረጃ ምንም ልዩነት የለ።

በፓርቲው ውስጥ ልዩነት አለ የሚሉ አመራሮች ካሉ በይፋ አደባባይ ወጥተው መናገር እንዳለባቸው አቶ በቀለ አክለው ገልጸዋል።

ኦፌኮ በቅርቡ ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር ስትራቴጂካዊ ጥምረት መፍጠሩን ተከትሎ እየበረታ መጥቷል በተባለ የፓርቲ አባላት አለመግባባት አንዳንድ አመራሮች ከሀላፊነት አስከመልቀቅ እንዳደረሳቸው የሚያመለክት መረጃ ከሰሞኑ መውጣቱ አይዘነጋም።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img