Sunday, October 6, 2024
spot_img

የ‹‹ሄር ኢሴ››ን ባሕላዊ ህግ በዓለም ቅርስነት ለማስመዘገብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 14፣ 2014 ― ‹‹ሄር ኢሴ›› የተባለን የኢሣ ማህበረሰብ ባሕላዊ ያልተጻፈ ሕግ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሣይንስና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) ለማስመዝገብ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጧል፡፡

ይህ የተገለጸው የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲና የሶማሌ ላንድ የኢሣ ማህበረሰብ አባቶች የተሣተፉበት በባህላዊ ህጎች ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ በድሬደዋ በተካሄደበት ወቅት መሆኑን የሶማሊ ክልል ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የሲቲ ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን ኃላፊ ወይዘሮ አያን አሊ ‹‹ሄር ኢሴ›› ባህላዊ መተዳደሪያ ህግ በሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን በ16ተኛው ክፍል ዘመን 44 የኢሣ ማህበረሰብ አባላት ተቀምጠው ያጸደቁት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የሶማሌ ህዝብ አንድ አካል የሆነው ኢሣ ማህበረሰብ ህጉን ከትውልድ ወደ ትውልድ በቃል እየተቀባበለ እየተመራበት እንደቆየ አስረድተዋል።

ህጉ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሶማሌ ላንድ የሚገኙትን የማህበረሰቡን አባላት ያስተሳሰረ መሆኑን ጠቁመው፣ ባህላዊ ህጉ ኢትዮጵያ ለምትገነባው የዘመናዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግብአትነት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

በአለም ቅርስት እንዲመዘገብ እየተሰራ መሆኑን ያመለከቱት ወይዘሮ አያን፤ ቅርሱ ሲመዘገብና ሲተዋወቅ የአፍሪካ ቀንድ ሃገራትን ይበልጥ ያስተሣስራል ነው ያሉት፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img