አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ መስከረም 12፣ 2014 ― ‹‹የታሪክ ንቅለ ምልከታ – ከኢማም አሕመድ እስከ ዳግማዊ ምንሊክ›› የተሰኘ ርእስ ያለው መጽሐፍ ለአንባቢያን ቀርቧል፡፡
በፋኢዝ መሐመድ የተሰናዳው ይኸው መጽሐፍ፣ በኢማም አሕመድ ኢብራሂም አል ጋዚ የድል ምሥጢሮች፣ የአመራር ብቃት እንዲሁም በአገራዊ የታሪክ መግባባት ዙሪያ የሚያተኩር መሆኑን ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡
ይኸው መጽሐፍ የፊታችን ዐርብ መስከረም 14 በታሪክ ጥናት እና ሌሎች ዘርፎች ሥመ ጥር የሆኑ የአገሪቱ ምሑራን እና አንባቢያንም ጭምር በተገኙበት እንደሚመረቅ ሰምተናል፡፡
የሥነ አዕምሮ ተመራማሪ እና የፍልስፍና ተማሪው ፋኢዝ ሙሐመድ በሀገረ አወስትራሊያ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ‹‹ሙስሊም ጠልነት በኢትዮጵያ›› በሚል ርእስ ባሳተሙት መጽሐፍና በተለያዩ የህትመት ሚዲያዎች ያቀርቧቸው በነበሩ መጣጥፎች በአንባቢያን ዘንድ ይታወቃሉ፡፡