Sunday, October 6, 2024
spot_img

በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ የሚያቀርቡ አምራቾች የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ተነሳ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― በባህላዊ መንገድ ወርቅ እያመረቱ ለባንክ የሚያቀርቡ አምራቾች ለክልሎች ሲከፍሉት የነበረውን የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ በሙሉ እንደተነሳላቸው የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሩ ታከለ ኡማ ገልጸዋል፡፡

ሚኒስትሩ ክልሎች ዘርፉን ለማበረታታት ባህላዊ ወርቅ አምራቾች ሲከፍሉት የነበረውን የሮያሊቲ ክፍያ ሙሉ ለሙሉ በማንሳታቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

የባህላዊ እና አነስተኛ ወርቅ አምራቾቻችን ለሀገራችን የማዕድን ክፍለ ኢኮኖሚ ዋልታ ሆነው ዘመናትን እያሻገሩን ይገኛሉ ያሉት አቶ ታከለ፣ እነሱን በተለያየ መንገድ መደገፍ፣ ከትከሻቸው ላይ ጫናዎችን ማቃለል ከእኛ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

የክልሎች ርእሰ መስተዳድሮች ለወሰዱት ተነሳሽነት ያመሰገኑት ሚኒስትሩ፣ ይህ እርምጃ ለባህላዊ የማዕድን ምርት እንደሀገር የሰጠነው ትኩረት ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ መልኩ ደግሞ በህገ ወጥ መንገድ የሃገር ሀብት ላይ አሻጥር ለሚሠሩት ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ስምምነት ላይ መደረሱንም የማዕድን እና ነዳጅ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል ።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img