Sunday, October 6, 2024
spot_img

ኢትዮ ቴሌኮም በ‹ቴሌ ብር› ከውጭ ሀገራት የሚላክ ገንዘብን የማስተላለፍ ፍቃድ አገኘ

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― ኢትዮ ቴሌኮም ‹ቴሌ ብር› በተባለው የሞባይል መገበያያ ዘዴው ከውጭ ሀገራት የሚላክ ገንዘብን የማስተላለፍ ፍቃድ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እንዳገኘ ካፒታል ጋዜጣ አስነብቧል።

ኩባንያው ባንድ ወር ጊዜ ውስጥ የ‹ቴሌብር› ደንበኞቹ ገንዘብ ከውጭ ለመቀበል የሚችሉበትን ሙከራ እንደሚያደርግ ዘገባው ጠቅሷል።

ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር በኢትዮ ቴሌኮም ይፋ የተደረገው ቴሌብር የተሰኘው አገልግሎት ገንዘብ ለመቀበል፣ ለመላክ፣ የግብይትና የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸም የሚውል ሲሆን፣ በአጭር ጊዜም አገልግሎቱን ለማግኘት ከ9 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች እንደተመዘገቡለት ኩብንያው አሳውቆ ነበር፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የተለመደ መሆኑ የሚነገረው በሞባይል የገንዘብ ማስተላለፍ፣ በጎረቤት ኬንያ ከተተገበረ 14 ዓመታት ያስቆጠረ ስለመሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ‘ኤምፔሳ’ የተሰኘው ይኸው የሞባይል ገንዘብ ሥርዓት አሁን ላይ 72 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ ነዋሪ እየተጠቀመው እንደሚገኝ ይነገራል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img