Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሱዳኑ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በሜ/ጄ ዐብደል ባቂ በክራዊ የተመራ ነው ተብሏል

የሱዳኑ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በሜ/ጄ ዐብደል ባቂ በክራዊ የተመራ ነው ተብሏል፡፡ በሜ/ጄ ዐብደል ባቂ በክራዊ የሚመሯቸው ወታደሮች በምስራቃዊ ሱዳን የሚገኘውን የሃሪቱን ጦር ተቆጣጥረው እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ወታደሮቹ ድልድዮችን መተላለፊያ መንገዶችን ይዘው እንደነበር የተገለጸም ሲሆን፣ የሃገሪቱን ብሔራዊ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ጣቢያን ለመቆጣጠር በሙከራ ላይ እንደነበሩም ነው የተገለጸው፡፡ ጣቢያው በዚሁ ወቅት መደበኛ ስርጭቱን አቋርጦ የተለያዩ ሃገራዊ ይዘት ያላቸውን ሙዚቃዎች ይለቅም ነበር ተብሏል፡፡

ኦምዱርማንን ከሃገሪቱ ዋና ከተማ ካርቱም የሚያገናኘው ድልድይም በአሁኑ ወቅትም ተዘግቶ ይገኛል፡፡ ሆኖም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው በቁጥጥር ስር መዋሉን የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ቃል አቀባይ ይህንኑ ነግረውኛል ብሎ አል ዐይን ዘግቧል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img