Sunday, October 6, 2024
spot_img

የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ንግግር በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ነቀፌታ ተሰነዘረበት

አምባ ዲጂታል፣ ማክሰኞ መስከረም 11፣ 2014 ― የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዳንኤል ክብረት ከሰሞኑ የሰነዘሩት አስተያየት በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ ነቀፌታ ተሰንዝሮበታል፡፡

በቃል አቀባዩ ኒድ ፕራይስ አደገኛ እና ተቀባይነት የለውም በተባለው ንግግር ዳንኤል ክብረት ‹‹ሰይጣን ከወደቀ በኋላ ሌላ ሰይጣን አልተፈጠረም›› በማለት ‹‹እነሱን የመሰለ ሰው መፈጠር የለበትም›› ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ አክለውም የልጆቻችን ማስፈራሪያ አድርገን መጠቀም አለብን፣ በተጨማሪም ‹ከታሪክ መዝገብ ውስጥ ተፍቀው መጥፋት አለባቸው›› ብለዋል፡፡

አዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዳንኤል ንግግሩን በተመለከተ እንዲያጠሩልኝ ጠይቄ በንግግሬ ‹‹እነሱ›› ያልኩት ‹‹አሸባሪውን የሕወሓት ቡድን ነው›› ሲሉ በጽሑፍ መልእክት መልሰውልኛል ብሏል፡፡

በዚሁ የአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ዘገባ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ቤልለኔ ሥዩም የዳንኤልን ንግግር ተከትሎ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትን የሰነዘረውን ነቀፌታ ወድቅ ማድረጋቸው ተመላክቷል፡፡

ባለፉት ጊዜያት የኢትዮጵያን ቋንቋዎች ባለመረዳት ተመሳሳይ ነገሮች መፈጠራቸውን ያስታወሱት ቤልለኔ፣ በሕወሃት ላይ የሚሰነዘሩ አስተያየቶች ‹‹ሆን ተብለው›› በትግራይ ሕዝብ ላይ የተባለ ተደርጎ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እንደሚውል ገልጸዋል፡፡

ቤልለኔ አክለውም የኢትዮጵያ መንግስት በቀዳሚነት ለትግራይ ሕዝብ ዘብ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ የሆኑት ዳንኤል ክብረት የሕወሃት ሰዎችን አስመልክቶ ሰጡት የተባለው አስተያየት በባህር ዳር ብሉናል ሆቴል ያደረጉት ነው፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img