Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሞጆ – መቂ – ባቱ የክፍያ መንገድ ሥራ ጀመረ

አምባ ዲጂታል፣ ሰኞ መስከረም 10፣ 2014 ― የሞጆ – መቂ – ባቱ 92 ኪሎ ሜትር የክፍያ መንገድ በዛሬው ዕለት ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡

የሞጆ ሐዋሳ የፍጥነት መንገድ አካል የሆነው የክፍያ መንገዱ፣ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሐብታሙ ተገኝ እና የትራንስፖርት ሚንስቴር ዲኤታ አቶ ካሣሁን ጎፌ በተገኙበት ነው ለአገልግሎት ክፍት የሆነው፡፡

የፍጥነት የክፍያ መንገዱ በ6 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ወጭ የተገነባ መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ለ7 አመታት ሲያስተዳድረው ከቆየው የአዲስ አበባ አዳማ እና የድሬደዋ ደወሌ የክፍያ መንገድ በመቀጠል ወደ ስራ የገባ 3ኛው የክፍያ መንገድ እንደሆነም ፋና ዘግቧል፡፡

መንገዱ በሚያዚያ ወር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መመረቁን ያስታወሰው ዘገባው፣ የክፍያ ቴክኖሎጂዎችን ለማሟላት ሲባል አገልግሎቱ መዘግየቱ በመርሃ ግብሩ መገለጹንም አስፍሯል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img