አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 7፣ 2014 ― በትግራይ ጦርነት ሁሉም የግጭቱ ተሳታፊዎች በቶሎ ለድርድር ከተቀመጡ፣ አሜሪካ ማዕቀቡን ልታዘገየው እንደምትችል ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ብሊንከን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት የተኩስ አቁም ንግግር ባስቸኳይ ካልተጀመረ የአሜሪካው ግምጃ ቤት መጠነ ሰፊ ማዕቀቦችን እንዲጥል በዛሬው እለት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
አሜሪካ ማዕቀብ ከጣለች የልማትና ሰብዓዊ ዕርዳታ እና የንግድ እንቅስቃሴዎች እንደማይካተቱ እንደሚደረግ የተጠቆመ ሲሆን፣ ቀውሱ በመጭው ሳምንት በተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ መወያያ እንደሚሆን ተነግሯል።
በሌላ በኩል ለሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደሚፈልጉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የአገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።