Sunday, October 6, 2024
spot_img

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለአሜሪካ መንግሥት ጥሪ አቀረቡ

አምባ ዲጂታል፣ ዐርብ መስከረም 7፣ 2014 ― በአሜሪካ አገረ ስብከት ያላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአሜሪካ ኮንግረስ በመገኘት የአሜሪካ መንግሥት የኢትዮጵያን ትክክለኛ ሁኔታ እንዲረዳ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ጫና እንዲተውም መጠየቃቸውም ነው የታወቀው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ትላንት በአሜሪካ ኮንግረስ ውይይትና ቆይታ አድርገው ነበር፡፡

በዋሺንግተን ዲሲው ውይይት በአሜሪካና በካናዳ የሚገኙ የ11 አኅጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ተካፍለዋል።

ለሁለት ቀናት ከተለያዩ የአሜሪካ መንግሥት ኃላፊዎች ጋራ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩት በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አህጉረ ስብከት የሚመሩ ሊቃነ ጳጳሳት የተሳካ ተልእኮ ማከናወናቸውን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ወደ አፋር እና አማራ ግዛቶች ባስፋፋው የጥፋት ጦርነት በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መገደላቸውን፣ መቁሰላቸውን እና መፈናቀላቸውን ለአሜሪካ ባለ ሥልጣናት የገለጹት አባቶች፣ የባይደን መንግሥት ትክክለኛ አቋም በመያዝ ሕወሐትን እንዳያስታምም ጠይቀዋል።

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img