Sunday, October 6, 2024
spot_img

በሕገ ወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተዋል ባላቸው ከ80 ሺሕ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ርምጃ መውሰዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና በህገወጥ ተግባር ውስጥ ሲሳተፉ ተገኝተዋል ባላቸው ከ80 ሺሕ 641 በላይ ተቋማት ላይ ርምጃ መወሰዱን የኢፌዲሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ የኮሙዩኒኬሽን አማካሪ አቶ ወንድአጥር መኮንንን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው፣ በህግ ማስከበር ዘመቻው ‹‹እየተገኘ ነው›› ያሉትን ድል ለመቀልበስ በህገ ወጥ ተግባራት ውስጥ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙ የንግድ ተቋማትን በመለየት ርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል፡፡

እንደ አቶ ወንድአጥር ገለጻ፤ ዶላርና ምርት የደበቁ፣ ያልተገባና ምክንያታዊ የሆነ የዋጋ ጭማሬ በማድረግ ለሕወሃት ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው፡፡

በዚሁ መሰረት 80 ሺህ 641 የንግድ ድርጅቶች ላይ የእገዳ፣ 520 የንግድ ድርጅቶች የንግድ ፈቃድ ስረዛ፣ 257 የንግድ ድርጅቶች ላይ የእገዳ እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑን የጠቆሙት አቶ ወንዳጥር፤ በሁለት ሺህ 230 የንግድ ተቋማት ላይ ክስ መመስረቱን ተናግረዋል፡፡

አቶ ወንዳጥር ያለምንም ኢኮኖሚያዊ ምክንያትና የአቅርቦት ችግር ያልተገባ ዋጋ በመጨመር ህገ ወጥ የሆነ ገንዘብ ለማጋበስ የሚሰሩ መኖራቸውንና በተለይም የህግ ማስከበር ዘመቻ እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት በዚህ ተግባር ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙ አካላትን መንግሥት እንደማይታገስም ገልጸዋል፡፡

ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከመረጃና ደህንነት፣ ከገቢዎችና ጉሙሩክ ባለስልጣንና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ በሚኒስትሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ እየተሰራ ነው ያሉት የኮሙኒኬሽን አማካሪው፤ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ አካላት ላይ የተጠናከረ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img