Sunday, October 6, 2024
spot_img

የሕወሃት ኃይሎች በአማራ ክልል ዳባት አካባቢ 120 ንጹሐን ዜጎችን መግደላቸው ተነገረ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― የሕወሃት ኃይሎች በአማራ ክልል 120 ሰዎችን መግደላቸውን ሬውተርስ የዜና ወኪል የአካባቢውን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ጥቃቱ የደረሰው ከዳባት ወረዳ አስር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የተባለ ሲሆን፣ የሕወሃት ታጣቂዎቹ ግድያውን የፈጸሙት የዛሬ ሳምንት ነሐሴ 27 እና በነጋታው ነሐሴ 28 መሆኑን የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም እና በአቅራቢያው የሚገኘው የጎንደር ከተማ አስተዳዳር ቃል አቀባይ ቻላቸው ዳኘው ገልጸዋል፡፡

120 አስከሬኖችን ማግኘታቸውን የገለጹ አስተዳዳሪው፣ የተገደሉት ሁሉም ገበሬዎች መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ እንደ አስተዳዳሪው ከሆነ አሁንም ደብዛቸው የጠፋ ሰዎች ስላሉ የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር ይችላል፡፡

ወደ አካባቢው አምርተው የቀብር ስፍራውን መጎብኘታቸውን ያመለከቱት የጎንደር ከተማ ቃል አቀባይ በበኩላቸው፣ ከምቾቹ መካከል ህጻናት፣ ሴቶች እና አዛውንቶች ይገኙበታል ብለዋል፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት በአካባቢው ለአጭር ጊዜ የቆዩት የሕወሃት ኃይሎች መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

ጥቃት አድርሷል በሚል የተከሰሰው የሕወሃት ኃይሎች ቃል አቀባይ ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ እንዳልሰጡት የዜና ወኪሉ አመልክቷል፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img