Saturday, November 23, 2024
spot_img

የታሰሩ ጋዜጠኞችን ጉዳይ በቅርበት ለመከታተል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር አሳወቀ

አምባ ዲጂታል፣ ረቡዕ ጳጉሜን 3፣ 2013 ― የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች ማኅበር ቀደም ሲል ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው እንዲሁም ትላንት ጳጉሜን 2፣ 2013 የናሁ ቴሌቪዥን የስፖርት ፕሮግራም ክፍል ባለደረቦች የሆኑት ጋዜጠኛ ግርማቸው እንየው እና አሸናፊ ዘለሌ በፀጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳውቋል፡፡

ባለሞያዎቹ ስለተያዙበት አካሄድ እና አሁን ስላሉበት ሁኔታ ከሚመለከታቸው አካላት መረጃ ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ያመለከተው ማኅበሩ፣ የሚመለከተው የመንግስት አካልም በተቻለ መጠን በፍጥነት ፍርድ ቤት የመቅረብ፣ የህግ ድጋፍ የማግኘት እንዲሁም የመጎብኘት መብታቸው እንዲጠበቅላቸው እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡

ማኅበሩ ጋዜጠኞች እንደማንኛውም ዜጋ ካጠፉ በህግ አግባብ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው የሚል እምነት እንዳለው በመግለጽ፣ በጋዜጠኝነት ሙያቸው ምክንያት ጋዜጠኞችን ማሳቀቅና ማዋከብ ግን ዜጎች መረጃ የማግኘት ነፃነትን የሚጨቁን ነው ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም መታሰሩ የተገለጸው ጌጥዬ ያለው ፍርድ ቤት በመዳፈር የተፈረደበት ሲሆን፣ ትላንት በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለጸው የስፖርት ጋዜጠኞቹ ግርማቸው እንየው እና አሸናፊ ዘለሌ የታሰሩበት ምክንያት እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡

ተዛማጅ ጽሑፍ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

ትኩስ ርዕስ

- Advertisment -spot_img